RSS

አማራ ክልል ወሎ መርሳ ከተማ

23 Apr

በአማራ ክልል በወሎ መርሳ ከተማ የሚኖሩ ሙስሊሞች ከአስር ሰላት ቡሀላ መንግስት በሙስሊሞች ላይ እያደረሰ ያለዉን የመብት ረገጣና በከተማቸዉ ሊዘጋጅ የነበረዉን የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም መንግስት በማገዱ አደባባይ በመዉጣት የከተማዎ ሙስሊሞች ተቃዉሟቸዉን ሲያሰሙ ከአካባቢዉ የፌደራል ፖሊሶች ጋር መጋጨታቸዉ ተሰማ:: በዚህም ግጭት የፌደራል ፖሊስ በወሰደዉ የሀይል እርምጃ በርካቶች በከፍተኛ ደረጃ ድብደባ እንደተፈፀመባቸዉ የአካባቢዉ ምንጮች ገለፁ:: በርካታ ሙስሊም ሴቶችና ወንዶችም ወደ ወልዲያ ከተማ ተወስደዉ መታሰራቸዉን ምንጮቻችን ገልፀዎል:: አላህ ይድረስላቸዉ!!!

 
Leave a comment

Posted by on April 23, 2013 in Uncategorized

 

Leave a comment