RSS

Author Archives: DimtsachinYisema

About DimtsachinYisema

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመንግሥትን የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት የምንቃወምበት ድምጽ

አስቸኯይ ማሳሰቢያ!!

አስቸኯይ ማሳሰቢያ!!
በታላቁ አንዎር መስጂድ ማንኛዉም ሙስሊም ለማደር ወደ መስጂዱ መሄድ እንደሌለበት በጥብቅ እናሳስባለን:: በዛሬዉ ስብሰባ መሠረት ማንኛዉም ሰዉ በመስጂዱ ማደር እንደሌለበትና የሱቢሂ ሰላትን ግን በአንዎር መስገድ እንዳለብን ብቻ ነዉ የተወሰነዉ:: ስለዚህ በመስጁ ወስጥ ለማደር የሄዳችሁ ሰዎች የኢሻ ሰላታችሁን ሰግዳችሁ ወደየቤታቹ ትመለሱ ዘንድ እናሳስባለን:: በመስጂዱ ማደር ለነዛ አረመኔዎች እራት ከመሆን በተጨማሪ የነገዉን ታላቅ ፕሮግራም እንዲያደናቅፍብን አመቺ ሁኔታ እንደምንፈጥር ማወቅ ይኖርብናል:: ይህንን መልዕክት በፍጥነት ወደ አንዎር መስጂድ ለማደር ለሚሄዱ ሰዎች እንድናስተላልፍ እንጠይቃለን!!!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized

 

ሐገር አቀፍ የአንድነትና የሰደቃዉ ፕሮግራም በነገዉ እለት ሀምሌ 8 በኢትዮጲያ ታላቁ አንዎር መስጂድ ይካሄዳል ተባለ::

ሐገር አቀፍ የአንድነትና የሰደቃዉ ፕሮግራም በነገዉ እለት ሀምሌ 8 በኢትዮጲያ ታላቁ አንዎር መስጂድ ይካሄዳል ተባለ:: ይህ ዉሳኔ የተላለፈዉ ዛሬ አዘጋጅ ኮሚቴዉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ከአዲስ አበባ ሙስሊሞች ጋር በታላቁ አንዎር መስጂድ ባደረገዉ ስብሰባ ነዉ:: ይህንን ፕሮግራም የተሳካ ለማድረግ ሙስሊሙ የሱቢሂ ሰላትን በታላቁ አንዎር መስጂድ በመስገድ በሩን ከመዘጋት እንዲታደግ ጥሪ አስተላልፈዎል:: በተጨማሪም ሱቢሂ ሰላት በአንዎር መስጂድ መስገድ ያልቻለ እስከ ጠዎቱ 2 ሰአት ድረስ አንዎር መስጂድ መድረስ እንደሚኖርበት መልዕክት ተላልፎል:: በነገዉ ሀገር አቀፍ የአንድነት እና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ መላዉ ሙስሊም መሳተፍ ስለሚኖርበት በስልክ ሜሴጅ እና በተለያዩ መንገዶች ጥሪ እናስተላልፍ ዘንድ እናሳስባለን:: አላህ ያሳካዉ!!!

 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized

 

አስቸኯይ ማሳሰቢያ

አስቸኯይ ማሳሰቢያ
የአፍሪካ የመሪዎች ስብሰባ የሚካሄድበት ቦታ መንግስት ሰዎችን አደራጅቶ በአካባቢዉ በማስረበሽ በቪዲዮ ለመቅረፅና በሚዲያ ለማቅረብ እየሰራ በመሆኑ በአካባቢዉ የምትገኙ ሙስሊሞች በአካባቢዉ ሊያደርጉት ላሰቡት ረብሻ ተሳታፊ ከመሆን ትቆጠቡ ዘንድ እናሳስባለን:: ይህንን መልእክት ላልሰሙት በፍጥነት እናሰማ!!

 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized

 

ትላንት ፌደራል ፖሊስ በአወልያ ንፁሀን ሙስሊሞች ላይ ጨለማን ተገን በማድረግ በፈፀመዉ ጭፍጨፉና ድብደባ የአወልያ የዉስጥ የመስጂዱ በሮች መሰባበራቸዉና ለአህ(ሱ.ወ) ሱጁድ የሚወረድበትን የመስጂዱ ምንጣፍ በጫማቸዉ በመግባት ድብደባ ሲፈፅሙ እንደነበር የተገለፀዉ:: በተመሳሳይም በቄራ ሰላም መስጂድ የፌደራል ፖሊሶች የመስጂዱን በር በመስበር መስጂዱ ዉስጥ የነበሩትን ንፁሀን ሙስሊሞችን ከነጫማቻዉ በመግባት ከፍተኛ ድብደባ መፈፀማቸዉ ነዉ የተገለፀዉ:: ጥይትም ሲተኩሱ የነበረ ቢሆንም በጥይት ተመቶ የሞተ ሰዉ እንደሌለ እና በድብደባዉ ግን በርካቶች መሰበራቸዉ ነዉ ከቄራ አካባቢ ምንጮቻችን የተገለፀል::

 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized

 

ትላንት ማታ በአዲስ አበባ ሙስሊሞች ላይ የተወሰደዉን አሰቃቂ ጭፍጨፉ ትዕዛዙን ያስተላለፈዉ ዶ/ር ሽፈራዉ እንደሆነ ምንጮቻችን አስታወቁ::

ትላንት ማታ በአዲስ አበባ ሙስሊሞች ላይ የተወሰደዉን አሰቃቂ ጭፍጨፉ ትዕዛዙን ያስተላለፈዉ ዶ/ር ሽፈራዉ እንደሆነ ምንጮቻችን አስታወቁ:: ትላንት ጁምአ ከሰአት ቡሀላ ዶ/ር ሽፈራዉ በአወልያ ስላለዉ ሁኔታ በስልክ አወልያ ዉስጥ ከነበሩ ድህንነቶች መረጃ በመቀበል ጠዎቱን በፖሊስ ማስፈራሪያ መግለጫ እንዲሰጥ ያደረገ ሲሆን ከሰአት ደግሞ የሰደቃዉ ፕሮግራም ከተሳካ የራሳቸዉን የምርጫ አስፈፃሚ መርጠዉ በረመዳን ወር ዉስጥ ሙስሊሙ የራሱን ምርጫ ስለሚያካሂድ እስከዛሬ የለፉንበት ገደል ሊገባብን በመሆኑ በአወልያ ማታ ላይ ብዙ ሰዉ ስለማያድርና ጭለማም ስለሆነ ማንም ሰዉ ከቤቱ ስለማይወጣ ጭለማን ተገን አድርገን ጥቃቱን እናድርስ በማለት የተወያዩ ሲሆን ከብዙ ክርክር ቡሀላ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በማሳበብ እርምጃ እንዉሰድ ብለዉ ተስማምተዉ የማታዉን ጥቃት እንዳደረሱ የዉስጥ ምንጮቻችን ገልፀዎል:: በአሁኑም ሰአት ማታ በህዝቡ ያልጠበቁት ተቃዉሞ ስለገጠማቸዉ ምን ማድረግ እንዳለባቸዉ እና በሚዲያም ምን ብለዉ ማቅረብ እንዳለባቸዉ እየተወያዩ ነዉ:: በዉይይታቸዉም የሽምግልና ሂደት ለማስጀመር እየተወያዩ እንደሆነና ህዝቡን ለማረጋጋትም ጥረት እንዲደረግ ትዕዛዝ አስተላልፈዎል:: በመላዉ ሀገሪቱም ባሉ ክፍለ ሀገሮች ህዝበ ሙስሊሙ ስብሰባ እንዲጠራና የማረጋጋት ስራ እንዲሰራ ለየክልሉ ደህንነት ክፍል መመሪያ መሰጠቱን ምንጮቻችን ገልፀዎል::የንፁሀንን ደም አፍሶለ መደራደር ማሰብ የሙስሊሞችን ደም ከማራከስ የሚመነጭ ነዉ!!

 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized

 

መላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ወደ ታላቁ አንዎር መስጂድ ጉዞ መጀመር ይኖርበታል::

መላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ወደ ታላቁ አንዎር መስጂድ ጉዞ መጀመር ይኖርበታል::ሙስሊሙም ይህን አዉቆ ወደ አንዎር መስጂድ እየተመመ ይገኛል:: በየቦታዉ በቡድን የምንጏዝ ከሆነ በየመንገዱ ጥቃት ለመሰንዘር ፖሊስ ስለሚመቸዉ በመነጣጠል ወደ አንዎር መስጂድ ጉዞ እንጀምር:: በየመንገዱ ፖሊሶች ለሚያደርሱብን ጭካኔ የተሞላ ጥቃት ፊት ለፊት ከመጋፈጥ በመቆጠብ በሰላም ወደ ታላቁ አንዎር መስጂድ እንድንገባ እናሳስባለን:: ወደ አወልያ ሚደረግ ጉዞ መኖር የለበትም!! ላልሰሙት አሰሙ!!!

 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized

 

በአዲስ አበባ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉን ጭፍጨፋ ላልሰሙት በማሰማት እናስተላልፍ::

በመላዉ ኢትዮጲያ የምትገኙ ሙስሊሞች ሆይ አሁን በአዲስ አበባ ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለዉን ጭፍጨፋ ላልሰሙት በማሰማት ነገ የሜሴጅ, ፌስቡክ መንገዶችን መንግስት ሊዘጋ ስለሚችል አሁኑኑ እናስተላልፍ:: ሁሉም ሙስሊም ነገ ስራ ከመግባት በመቆጠብ በአንድነት መብታችንን ለማስከበር መነሳት ይኖርብናል:: አሁን ሁሉም ወደየመስጂዱ እንዲመለስ ጥሪ እናስተላልፍ!!!

 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized