RSS

ሐገር አቀፍ የአንድነትና የሰደቃዉ ፕሮግራም በነገዉ እለት ሀምሌ 8 በኢትዮጲያ ታላቁ አንዎር መስጂድ ይካሄዳል ተባለ::

16 May

ሐገር አቀፍ የአንድነትና የሰደቃዉ ፕሮግራም በነገዉ እለት ሀምሌ 8 በኢትዮጲያ ታላቁ አንዎር መስጂድ ይካሄዳል ተባለ:: ይህ ዉሳኔ የተላለፈዉ ዛሬ አዘጋጅ ኮሚቴዉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ከአዲስ አበባ ሙስሊሞች ጋር በታላቁ አንዎር መስጂድ ባደረገዉ ስብሰባ ነዉ:: ይህንን ፕሮግራም የተሳካ ለማድረግ ሙስሊሙ የሱቢሂ ሰላትን በታላቁ አንዎር መስጂድ በመስገድ በሩን ከመዘጋት እንዲታደግ ጥሪ አስተላልፈዎል:: በተጨማሪም ሱቢሂ ሰላት በአንዎር መስጂድ መስገድ ያልቻለ እስከ ጠዎቱ 2 ሰአት ድረስ አንዎር መስጂድ መድረስ እንደሚኖርበት መልዕክት ተላልፎል:: በነገዉ ሀገር አቀፍ የአንድነት እና የሰደቃ ፕሮግራም ላይ መላዉ ሙስሊም መሳተፍ ስለሚኖርበት በስልክ ሜሴጅ እና በተለያዩ መንገዶች ጥሪ እናስተላልፍ ዘንድ እናሳስባለን:: አላህ ያሳካዉ!!!

 
Leave a comment

Posted by on May 16, 2013 in Uncategorized

 

Leave a comment