RSS

አህባሽ በጎንደር ከተማ እንቅስቃሴውን በአዲስና በተጠናከረ መልኩ መንቀሳቀስ መጀመሩን የጎንደር ዘጋቢያችን አስታወቀ

23 Apr

ዜና ጎንደር
አህባሽ በጎንደር ከተማ እንቅስቃሴውን በአዲስና በተጠናከረ መልኩ መንቀሳቀስ መጀመሩን የጎንደር ዘጋቢያችን አስታወቀ፡፡ አህባሽ በአሁኑ ሰዓት እየከሰመ ባለበት ወቅት ጎንደርንና አካባቢዋን የመጨረሻው ምሽጉ በማድረግ የሞት ሽረት ትግሉን እያደረገ ይገኛል፡፡የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብ ታላላቅ መሻዒሆች፣ አሊሞች ና ዳዒዎች የፈለቁበትሲሆን አህባሾች ግን ህብረተሰቡ ምንም ዕውቀት እንደሌለው በማሰብ የኢትዮጵያ ታላላቅ ዳዒዎችን እንደነ ኡስታዝ በድሩ ሁሴንን፣ ኡስታዝ ያሲን ኑሩን፣ኡስታዝ ሀሰን ታጁንና ሌሎች ታላላቅ ዳዒዎችን በተለመደው ቅጥፈታቸው በማክፈርና በዘመኑ የማስፈራሪያ ጭራቃዊ ቃል በ “ውሀብያ” በመፈረጅ መሻዒሆችን ያከፍራሉ፣ስለዚህ የእነርሱን ካሴቶች ማየትም ሆነ መስማት ወንጀል ነው የአፍሪካ ቲቪንም ማየት ወደ ጥመት እንደሚወስድ በሰፊው እየተቀሰቀሰ መሆኑ ታውቋል፡፡ በአህባሽ የሰሜን ጎንደር ፊታውራሪ ሙስጦፋ አሚኑ የሚመራው ይህ ነውጠኛ ኢስላማዊ አንጃ ጠቀም ባለ ገንዘብ በመደለል አህባሽን ወደ ጎንደር እንዲገባ በ2001 ተዋውለው ከመጡትና በአሁኑ ወቅት የጎንደር ከተማ ዑለማ ምክር ቤት የዳዕዋ ዘርፍ ሀላፊነትን በጉልበት የያዘውና በጥንቆላ ሙያ የሚተዳደረው ኑርሁሴን ዳውድ የተባለው ግለሰብ ጁምዐ በጎንደር ከተማ በቀበሌ 11 በሚገኘውና በርካታ ታዋቂ ዳዒዎችን ባፈራው መስጊድ በመገኘት ለሰላት የመጣውን ህዝብ ያሳዘነ፣ያስቆጣና ህዝበ ሙስሊሙን ያቃጠለ ንግግር ማድረጉ ታውቋል፡፡ ”ውሀብያ” ብሎ የጠራቸው ግለሰቦች በጅማ ፈጸሙት ስላለው ጉዳይም ተረተረት ማሰማቱ ን ከስፍራው ጠደረሰን ዘገባ ይጠቁማል፡፡ በሰላ ምላሱ ዘወትር የጎንደርን ሙስሊም ሲያደማ የኖረው፣ከአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች በሙስናና በማጭበርበር ቅሌት የተባረረው፣በጥንቆላ ሙያ ተሰማርቶ የሚገኘውና በአሁኑ ወቅት ደግሞ ከአህባሽደጎስ ያለ ገንዘብ ከተሰጣቸውና በማን አለብኝነት በየመስጊዱ ህዝበ ሙስሊሙን አንጀት በማሳረር ላይ ከሚገኙት የሙስጦፋአሚኑ ቀኝ እጅ የሆነው ኑርሁሴን ዳውድ ባሰማው ድስኩር ስለ ውሀብያ ካፊርነት ከደሰኮረ በኋላ “በጅማ አንድ ወጣት እናቱ ሁልጊዜ የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዓ.ወ)መውሊድን ታወጣ ነበር፡፡ ወጣቱ “ከውሀብያዎችን” ትምህርት ከተሰጠው በኋላ እናቱ ሁሌ የነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዓ.ወ) መውሊድ ታወጣለች፡፡ስለዚህ ምን ላድርጋት ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱምአንገቷን ሰይፋት አሉት፡፡ ወጣቱም እንደተባለው ሄዶ እናቱን አንገቷን በሰይፍ ቆርጦ ጣላት፡፡ ውሀብያ ብሎ ማለት እነዚህ ናቸው፡፡ እናታቸውን መውሊድ ስላወጣች የሚሰይፉ፡፡ ስለዚህ ወደፊት ለሚደረገው ምርጫ እነዚህን ሰዎችእንዳትመርጡ መምረጥ ያለባችሁ ያገራችን ሸህ አስተምሮትን የተቀበሉ “የአህባሽን አስተምሮት ማለት ነው እነርሱን ምረጡ” በማለት ማሳሰቢያ ቢጤ በመጨመር ድስኩሩን አጠናቋል፡፡ ለጁምዓ ሰላት የመጣው ህዝብ ማጎምጎም ጀመረ፡፡ሁሉም ሰላቱ እስኪያልቅ ቸኮለ፡፡ ግቢው በውካታ ተዋጠ፡፡አንዳንድ ያነጋገርናቸው ሙስሊሞችም እኛ አንድ ነን ለምን እነደ ህጻን ያታልሉናል ለምንስ አዕምሯችን ያደሙታል በማለት በምሬት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸውልናል፡፡ አንዳንዶችም ዲናችን መቀለጃ አይደለም ስለዚህ ከእንደዚህ አይነት የማጭበርበር ጉዳይ መቆም አለበት ብለዋል፡፡ ወጣት ሙስሎሞችም ነገሩ ጎንደር ላይ ለምን በረታ በማለት የጠየቁ ሲሆን እንደ ወሎየዎች የሰደቃ ፕሮግራም በማዘጋጀት አንድ መሆናችንን መግለጽ አለብን በማለትበምሬት ይናገራሉ፡፡አህባሽም ጎንደርን ምሽግ አያደርጋትም በማለት በቁጭት ተናግረዋል፡፡ የአንድ ብር ለአንድ ጁምዓም ገቢ በእጅጉ ያቆለቆለ መሆኑን የብሩ ሰብሳቢዎች ኮሚቴ አስታውቀዋል፡፡ አንዳንድ ሰብሳቢዎች እንደገለጹት በሚቀጥለው ሳምንትም በዚሁ ሊቀጥል እንደሚችልና ይህ ዓይነት ኡማውን ሊከፍልየሚችል ንግግር እንዶቆም ለመስጊድ አስተዳደሩ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡ እኔም የዛሬውን ዘገባየን በዚሁ ላብቃ፡፡ አላህ በኸይር ያሰንብተን›››

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 23, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: