RSS

በአወልያ የፊታችን እሁድ ሀምሌ 8 የሚካሄደዉን ሀገር አቀፍ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራሙን ለማክሸፍ መንግስት በተለይም የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑ ታወቀ

23 Apr

በአወልያ የፊታችን እሁድ ሀምሌ 8 የሚካሄደዉን ሀገር አቀፍ የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራሙን ለማክሸፍ መንግስት በተለይም የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑ ታወቀ:: ባለፈዉ ሀሙስ በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን በትላንትናዉ እሁድ የተካሄዱትን የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ለማክሸፍ ወስነዉ የነበረ ሲሆን በየቦታዉ የነበረዉ እንግልትና እገታ በፌደራል ጉዳዮች የተሰጠ ትዛዝ መሆኑ ታዉቆል:: እሁድ እለት የተካሄዱትን የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም ማክሸፍ ከቻልን የአወልያንም የአንድነትና የሰደቃ ፕሮግራም በእርግጠኝነት ማክሸፍ እንችላለን በማለት የፌደራል ጉዳዮች አቅዶ የነበረ ቢሆንም በሀያሉ አላህ (ሱ.ወ) እገዛ ሙሉ ለሙለ የፌደራል ጉዳዮች ሴራ መክሸፍ ይታወሳል:: በዚህም የተነሳ መንግስት እጅጉን የተበሳጨና ያፈረ ሲሆን በተጠናከረ መልኩ የአወልያን የሐምሌ 8 ፕሮግራም ለማጨናገፍ ቆርጦ ተነስቷል:: በዚህም ከሁሉም ክልሎች የፀጥታና የደህንነት ሀይሎች ጋር የፌደራል ጉዳዮች በመቀናጀት ከአዲስ አበባ ዉጪ የሚገኙ ከተሞች ላይ ሙስሊሙ ፕሮግራሙን እንዳይካፈል በተለያየ ዘዴ እንዲያስቀሩት ታዘዎል:: በአዲስ አበባም ትላልቅ እናቶች አባቶች በፕሮግራሙ ላይ እንዳይካፈሉ ለማድረግ ከፍተኛ የቤት ለቤት ቅስቀሳ መጀመራቸዉ ታዉቖል:: እንዲሁም በፕሮግራሙ ላይ ታላላቅ ሰዎችም እንዳይገኙ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛሉ:: በሚያስገርም ሁኔታም ካልሆነ የአወልያን በር እንዝጋባቸዉእና ፕሮግራሙን እናስቀረዉ በማለትም ሲመካከሩ እንደነበር የዉስጥ ምንጮቻችን ገልፀዎል:: በተጨማሪም መንግስት ረመዳን ከመግባቱ በፊት ሴቶችን በየቤቱ በማሰማራት እና ኑ ቡና ጠጡ በሚል ሽፉን የመጅሊስ አመራሮች ምርጫ በቀበሌ ይሁን እንበል:: ሀይድ ላይ ከሆንን መምረጥ አንችልም በማለት ሙስሊም እናቶችን እና እህቶችን መደለል መጀመራቸዉ ተገልፆል:: እንዲሁም ኦሞ, ስኯር,እና ሳሙናም በመስጠት ትላልቅ እናቶችን የመደለል ስራ እየተሰራ ሲሆን አላማዉም ሴቶች ከተቀበሉን ቤታቸዉ ያለዉን ወንድ መቀየር ይችላሉ ተብሎ በመታመኑ ነዉ:: እዉን ከአላህ ጋር መታገል ያዎጣቸዉ ይሆን?? አላህ ሴራቸዉን ያክሽፍባቸዉ!!! ሁላችንም እንደተለመደዉ ይህንን መረጃ ላልሰሙት በማሰማት ኢስላማዊ ግዴታችንን እንወጣ!!!!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 23, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: