RSS

በመላዉ አለም የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያዉያን ሙስሊሞች በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ የወከሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከታሰሩበት ማዕከላዊ ተለቀቁ

23 Apr

በመላዉ አለም የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያዉያን ሙስሊሞች በፊርማቸዉ አረጋግጠዉ የወከሉት የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል ከታሰሩበት ማዕከላዊ ተለቀቁ:: ከጠዎቱ 3 ሰአት ላይ ኡስታዝ አቡበከር እና ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አብረዉ በመኪና እየተጏዙ በነበረበት ወቅት አንድ መኪና በከፍተኛ ፍጥነት ወደነሱ መኪና በመምጣት መንገድ ዘግቶባቸዉ ይቆማል:: ወድያዉኑ አራት ሰዎች በፍጥነት ከመኪናዉ በመዉረድ ወደነ ኡስታዝ አቡበከር በመምጣት ኑ ዉጡ በማለት ያንባርቁባቸዎል:: እነሱም መኪና ዉስጥ እንዳሉ ማንነታቹን ሳናዉቅ አንወርድም ሲሏቸዉ ከአራቱ ሰዎች አንዱ የኡስታዝ አቡበከርን መኪና በር በሀይል ለመበርገድ ሙከራ አደረገ:: ማንነታችሁን ከገለፃችሁልን ከመኪናዉ እንወርድላቹኃለን ሲሏቸዉ የፖሊስ መታወቂያቸዉን በማሳየት ከመኪናዉ አስወርደዉ በራሳቸዉ መኪና ጭነዎቸዉ ማዕከላዊ ጎን በሚገኘዉ አዲሱ የአ.አ ፖሊስ ኮሚሽን ህንፃ ይወስዷቸዎል:: እዛ ከደረሱም ቡሀላ ሁለ ነገራቸዉን የተቀበሏቸዉ ሲሆን ቀበቷቸዉንም ሳይቀር አስወልቀዎቸዉ ነበር:: ሁለቱንም ለየብቻ የተለያየ ክፍል አስገብተዉ ያስቀመጡዎቸዉ ሲሆን ኡስታዝ አቡበከር አህመድን ከዚህ ቡሀላ በኢትዮጲያ ዉስጥ ለሚፈጠረዉ ችግር በሙላ ተጠያቂዉ አንተ ነህ:: የፊታችን ሐምሌ 8 በአወልያ ይካሄዳል በተባለዉ ፕሮግራም ላይ ለሚፈጠረዉ ከባድ ችግር ሀላፊነቱን የምትወስደዉ አንተነህ በማለት ዛቻ እና ማስፈራሪያ ተሰቷቸዎል:: ቀጥለዉም ሁለቱንም አንድ ክፍል በማስገባት ሁለት የፀጥታ ሀይሎች ዛቻና ማስፈራሪያቸዉን ተያያዙት:: እናንተ ሀገሪቱን ለማተራመስ እየተንቀሳቀሳቹ ትገኛላቹ:: ከኢትዮጲያ ፀረ ሰላም ሀይሎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዳላቹ በተጨባጭ ደርሰንበታል:: ህገ ወጥ ናችሁ:: በሰደቃ ስም ሀገሪቱን እያመሳችሁት ገኛላችሁ:: ከዚህ ቡሀላ ማንኛዉም አይነት ሰደቃ የሚባል ፕሮግራም እንዳንሰማ:: ከዚህ ቡሀላ ኮሚቴ ነን የምትሉትን አማርኛ አቁሙ:: እናንተ ህገ ወጦች ናችሁ በማለት ማስፈራሪያቸዉን ለመቀጠል ሲሞክሩ ጀግኖቹ የኢስላም ልጆች እኛ ህገወጥ አይደለንም:!!! ህገ ወጥ እናንተናችሁ በማለት አይደለም ማስፈራሪያቸዉን ሊቀበሉ ይቅርና ያለአንዳች መደናገጥ ፅናታቸዉን አሳዩዎቸዉ:: አስፈራሪዎቹም ጩኸታቸዉን ቀጠሉ እጅግ በጣም ተቆጡ:: እኛ እኮ እዚህ ያመጣናችሁ ለስብሰባ አይደለም:: እናንተን አንድም ሙስሊም አልመረጣችሁም:: ህዝብ በድምፁ የመረጠዉ ኢህአዴግን ብቻ ነዉ:: ከዚህ ቡሀላ ኮሚቴ የሚባል ነገር መንግስት አይቀበለዉም:: መንግስት ዝም ሲላችሁ የፈራችሁ መስላችሁ ወይ?? ከዚህ በላይ መንግስት አይታገሳችሁም:: ሀገሪቱን ወደ አላስፈላጊ ነገር እየመራችኃት ስለሆነ በዝምታ አናያችሁም!! ከዚህ ቡሀላ የምናስራችሁ ወይም ፍርድ ቤት የምናቀርባችሁ እንዳይመስላችሁ:: መንግስት የራሱን እርምጃ እንደሚወስድባችሁ እወቁ በማለት ማስፈራሪያቸዉን አዥጎደጎዱት:: የሙስሊሙ ኮሚቴዎችም ያላአንዳች ፍርሀት አስደናቂ ምላሻቸዉን ሰጡ:: እባካችሁ ይህንን ማስፈራሪያችሁን ተዉ!! እኛ የምንፈራችሁ መስሏቹ ከሆነ አትሳሳቱ:: አንድም እናንተን የምንፈራበት ምክንያት የለም:: ለምን አስካሁን እርምጃ አትወስዱብንም ነበር:: ይኸዉ አሁን አጠገባችሁ ስለሆንን ቀጠሮ ለምን ትሰጣላችሁ!! እዚዉ የፈለጋችሁትን እርምጃ ዉሰዱ::እኛ ሞትንም ሆነ እስራትን የምንፈራ አይደለንም:: በማለት ኢስላም ምን ያህል ፅናት እንደሰጣቸዉ አሳይተዎቸዎል:: ይህንን ማስፈራሪያቸዉን ባዶ ካስቀሩባቸዉ ቡሀላ ኡስታዝ አቡበከር አህመድን በቅድሚያ የለቀቁት ሲሆን ከቆይታ ቡሀላም ኡስታዝ አህመዲን ጀበልን አዘግይተዉ ለቀዉታል:: ኢስላም ሂወታችንን አሳልፈን የምንሰጥለት ሀይማኖት መሆኑን ዘነጉት እንዴ??? አላሁ አክበር!!!!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 23, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: