RSS

ኮምቦልቻ ልዩ ትዝታ ጥላ አለፈች!

20 Apr

ኮምቦልቻ ልዩ ትዝታ ጥላ አለፈች!

የዚህ ፅሁፍ አዘጋጅ ያሳረፋቸው ቃላት በዛሬው እለት የተከሰተው በውስጡ ያሳደረበትን ስሜት ይገልጣል ማለት ያስቸግራል፡፡ ለማንኛውም የሚከተለው (ማለትም እሁድ ሐምሌ 1 2004) በኮምቦልቻ ሆኗል፡፡

ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች አንድ ዓመት የሞላውን ፈተና መጋፈጥ ከጀመሩ ጊዜ አንስቶ ጥያቄዎቻቸውን ህጋዊ ሥርዓቱን በተከተለ መልኩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል አቅርበው ከዳር እስከ ዳር የተነቃነቁ ቢሆንም ከጥቂት ጊዚያት ወዲህ ጥያቄው የህዝበ ሙስሊሙ ሳይሆን የጥቂት “አክራሪዎች፣ ፅንፈኞች…” ነው በሚል ሙስሊሙን ዜጋ “ነባር” እና “መጤ” በማለት ለመከፋፈል ከፍተኛ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በሚካሄድበት በዚህ ወቅት ሙስሊሙ ዜጋ ይህንን በመቃወም እኛ ሙስሊሞች ነን፣ አንድ ነን፣ አንለያይም በማለት ከሦስት ወራት ወዲህ በመላ ኢትዮጵያ የአንድነት ፕሮግራም፣ ከዚሁም ጋር ተያይዞ ይህ ሙሲባ የመጣብን በራሳችን ወንጀል በመሆኑም ፈጣሪያችን ምህረቱን እንዲቸረን በማሰብ የሶደቃ ዝግጅት በአንድላይም የአንድነት እና የሶደቃ ዝግጅት በሰፊው እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የወሎ ምድር ኮምቦልቻ ከተማ በዛሬው ዕለት አስተናግዳ የዋለችው ዝግጅትም የዚሁ ክፍል ነው፡፡
የኮምቦልቻው ፕሮግራም ከእወጃው ጀምሮ እስከ ዛሬው የጧት ክፍለ ጊዜ ድረስ የብዙዎችን ትኩረት ከመሳቡም በላይ አሳሳቢም ነበር፡፡
ኮምቦልቻ ከተማ ከደሴ 25 ኪሎ ሜትሮችን ብቻ ርቃ የምትገኝ ብትሆንም በደሴ የሙስሊም ህብረተሰብ እና በኮምቦልቻ ሙስሊም ህብረተሰብ መካከል ልዩነቶች እንዳሉ ይነገራል፡፡ የአሕባሽ ፊትና አገራችን ከገባ በኋላ ኮምቦልቻ የአሕባሾች ማዕከል ተደርጋ ተወስዳ የመንግስት ከፍተኛ እገዛ ታክሎበት አሕባሾች እንደልባቸው ሲፈነጩባት ቆይተዋል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በሌሎች አካባቢዎች የታየውን የደመቀ ዝግጅት በኮምቦልቻ ማካሔድ አዳጋች እንደሚሆን ግምት የተወሰደው ቀደም ሲል ነበር፡፡
ይሁንና በወኔ የተሞሉ የከተማዋ ሙስሊሞች እነኚህን ሁሉ ፈታኝ አጋጣሚዎች ችላ በማለት እና በጎረቤት ወንድሞቻቸው እየታገዙ ሙስሊሙን ኡማ ወደ አንድ መድረክ የመጥራቱን ተግባር ተያያዙት፡፡ እንዲህ እንዲህ እያለ ውጥረቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሰበት የትላንትናው ቅዳሜ እና ዛሬው እሁድ ቀናቶች ደረሱ፡፡
የፕሮግራሙ አዘጋጆች የጥሪ አዋጁን ሀረጎ ላይ ሆነው የጎሰሙት ይመስል ከአራቱም የኮምቦልቻ አቅጣጫዎች (በደሴ በኩል ፡- ከደሴ፣ ገራዶ፣ ሐይቅ፣ እስከ ወልዲያ፣ ከሐርቡ በኩል ሐርቡ፣ ከሚሴ እስከ አዲስ አበባ፣ ከባቲ በኩል ከደጋን፣ ገርባ፣ባቲ ኤሊ ውሃ፣ ሎጊያ፣ እስከ ሠመራ እንዲሁም ከኮምቦልቻ ገጠራማ አካባቢዎች በሁሉም አቅጣጫዎች) ሰዉ መጉረፍ የጀመረው ገና በማለዳ ነበር::
ደሴ መነኻሪያን ካፍ እስከ ገደፉ የሞላው ተጓዥ መኪና እንደማያገኝ ቀደም ሲል ቢገነዘብም መኪና እንደተከለከለ ቁርጡን ባወቀ ቅፅበት የወሰደው እርምጃ እጅግ ልብ የሚነካ ነበር፡፡ በጥቅል በጥቅል እየሆነ ከግቢው በመውጣት ዋና ጎዳናውን ተከትሎ 25 ኪሎ ሜትሩን በእግሩ ለማቆራረጥ ወደ ሀረጎ ገደላማ መንገድ አመራው፡፡ ወደ ጫካው ተመመ፡፡ በዚህ ጉዞ ላይ እናቶች እና ሕፃናቶች መኖራቸው ልብ የሚነካ ሲሆን በአንጻሩ የመንግስትን ጭካኔ ፍንትው አድርጎ አሳይቷል፡፡ በዚህ ጉዞ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተሳትፈውበታል፡፡ መንገዱን በአንዴ ፉት እንዲሉት ከፍተኛ እገዛ ያደረገላቸው በህብረት እያሰሙት የነበረው እልክ የተሞላበት የተክቢራ ድምጽ ነበር፡፡ የክልሉ ፈጥኖ ፖሊሶች እና መደበኛ ፖሊሶች የእግር ጉዞውን ለማስቆም ቢጥሩም ጉዳዩ ከቁጥጥራቸው ሊወጣ እንደሚችል ሲገነዘቡ መንገዱን በመልቀቅ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ አድርገዋቸዋል፡፡ በዚህም በድል ስሜት በእግራቸው ተጉዘው የፕሮግራሙ ተካፋይ መሆናቸውን አረጋገጡ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ከባቲ፣ ደጋን እና ገርባ ከ27 መኪናዎች በላይ ተጭነው ሲመጡ መንገድ ላይ በፌዴራል ፖሊስ ቢታገቱም ሁሉም ከመኪናቸው በመውረድና ተሰባስበው ሲያበቁ ክንድ ለክንድ በመቆላለፍ የተክቢራ ድምጽ በማሰማት በፖሊስ የታጠረውን መስመር ሰብረው በማለፍ በእግራቸው ተጉዘው እነሱም የፕሮግራሙ ታዳሚ መሆናቸውን አስመሰከሩ፡፡
በሀርቡ መስመርም ይኸው የተከሰተ ሲሆን ከ30 በላይ የሚሆኑ መኪናዎች እንዳይገቡ በማድረግ መጉላላት የተፈጠረ ሲሆን አብዛኛው በእግሩ ተጉዞ ወደ ፕሮግራሙ አምርቷል፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ሸኸ ሙሐመድ ኃምይዲን፣ ዳዒ ባሕሩ እና ሌሎችም የእገታው ሰለባ እንደነበሩ ትላንትናውኑ ለማሳወቅ ችለናል፡፡
ይህን ሁሉ መሰናክል አልፎ እውን የሆነ ፕሮግራም ድምቀቱ ምን ይመስል ነበር ብላችሁ መጠየቅ አምሯችኋልን? ራሳችሁ መልሱ፡፡
እንደማንኛውም የሶደቃ እና የአንድነት ፕሮግራሞች ተመሳሳየ ይዘት የነበረው ዝግጅት የቀረበ ሲሆን የነበረው የታዳሚ ቁጥር እጅግ የበረከተ መሆኑ ተስተውሏል፡፡ ፕሮግራሙ በሰላም ተካሔዶ በ ሠላም ተጠናቋል፡፡
ከፕሮግራሙ መጠናቀቅ በኋላ ከአዲስ አበባ የመጡት እንግዶች ያረፉበት አካባቢ የፖሊስ ኃይሎች መብዛት የተስተዋለ ሲሆን በስተመጨረሻ የህዝበ ሙስሊሙ ተወካይ ሸኽ መከተ ሙሔ መታሰራቸው ተገለጠ፡፡ (በአሁኑ ሰዓት ደሴ ከወሰዷቸው በኋላ ተለቀዋል፡፡)
አላሁ አዕለም

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 20, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: