RSS

አሕባሽን ለማጠናከር የሱፍያ ማህበር እና አህለሱና በማለት ያቋቋሙትን ስብስብ ሰኞ ሰኔ 18 2004 ማዘጋጃ ቤት ስብሰባ ጠርተው ነበር

15 Apr

አሕባሽን ለማጠናከር የሱፍያ ማህበር እና አህለሱና በማለት ያቋቋሙትን ስብስብ ሰኞ ሰኔ 18 2004 ማዘጋጃ ቤት ስብሰባ ጠርተው ነበር፡፡ የአህባሽ አቀንቃኝ ናቸው ተብለው የሚታሰቡት ወደ 250 ሰዎች የተጠሩ ሲሆን 150 የሚሆኑቱ ተገኝተዋል፡፡ የፌዴራል መጅሊስ የዑለማ ምክር ቤት ፀሐፊ ኢዘዲን የአስመራጭ፣ የሥራ አስፈፃሚ እና አባላት ጠቋሚ በመሆን ስም ዝርዝር ያቀረበ ሲሆን 
ከአስመራጮች 
1. አቶ ታደለ ደሳለኝ
2. ሸህ መዚድ
3. ሸህ ዓብዱል መሊክ ቀርበዋል፡፡
ከሥራ አስፈፃሚ ውስጥ፡ 
1. የገታው ሸኽ ልጅ የሆኑት ሸኽ ያቁት ሙህዲን ሊቀመንበር ( እሳቸውን ሊቀመንበር ያደረጉበት ምክንያት እሳቸውን ከፊት በማስቀመጥ ሌሎች ሱፊዮችን እናስገባለን በሚል መሆኑ ታውቋል) 
2. ም/ል ሸህ ሙሀመድ ኑር ምክትል ሊቀመንበር የተደረጉ ሲሆን
3. የትግራይ ብሔር ተወላጁ እና ከዚህ ቀደም በሴኩሪቲ ሥራ ላይ ተሠማርቶ የነበረው መ/ር ሙሐመድ ዩሱፍ ዓለሙ ፀሐፊ ሆኖ ተሰይሟል፡፡
ከአባል ደግሞ 
4. አህመድ ኢብራሂም ከአቃቂ ክ/ከተማ 
5. አወል ላለምዳ ከአቃቂ ክ/ከተማ
6. መሀመድ አሚን ከንፋስ ስልክ ላፍቶክ/ከተማ
7. ዓብዱረህማ አል- ፈቂ 
8. ሙሐመድ ኑሪ አል ፈቂ 
9. ዑስማን ረዲ
የዑለማ ምክር ቤቱ ፀሐፊ ኢዘዲን ንግግር ባደረገበት ሰዓት ምርጫ ይደረጋል፣ በምርጫውም የኛ ሠው እንጂ ሌላ አይመረጥም ያለ ሲሆን በእጁ የያዘውን መመሪያም ገልጦ አንብቧል፡፡ ነገሩ የተካሄደው እጅ በማውጣት ሳይሆን በያዘው የስም ዝርዝር ስማቸውን በመጥራት እና ሰዎቹን ወደ መድረክ ይዞ በመውጣት አጽድቁልን የሚል ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ ታዳሚው ሲያጨበጭብ ከዚህ ቀደም ለነኚሁ አካላት ብዙ ስራ ሲሰራላቸው የቆየ እና በዛሬው ሂደት ላይ እንደሚመረጥ እርግጠኛ ሆኖ የተገኘ “በድር ኢብራሒም” የተሰኘ ግለሰብ ከተቀመጠበት በመነሣት እንዴት እንደዚህ ዓይነት ምርጫ ይደረጋል? ይህ አካሄድ ትክክል አይደለም፡፡ ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት እንጂ በዚህ መልኩ መሆን የለበትም በማለት ረብሻ ሲፈጥር በሴኩሪቲ አካላት ተይዞ አዳራሹን እንዶለቅ ተደርጓል፡፡ይህ ግለሰብ ከዚህ ቀደም ፈትህ መስጂድ አባቦራ አካባቢ እና በየቦታው በመበጥበጥ የሚታወቅ ሲሆን አንዋር መስጅድም ስድብ የተሞላበት ዳዕዋ በማድረጉ ተይዞ ታስሮ ውቃል፡፡
ይህንን አደረጃጀት በየክ/ከተማው ለማዋቀር የሚፈለግ ሲሆን ከምርጫው በስተፊት እነዚህ ሰዎች ተጠናክረው ታች ድረስ እንቅስቃሴ አድርገው ቢሮ ከፍተው እንዲንቀሳቀሱ ይፈለጋል፡፡ ለምርጫውም ስራ እንዲሠሩና ተሳክቶላቸው የመጅሊስ ምራጫ ሙሉ ለሙሉ እንደሚፈለለገው ከሆነ እሰየው፣ በተናጠል አህለሱና ተብሎ ሱፍያዎችን ለማያዝ እቅድ አላቸው፡፡ የመጅሊስ ነገር ስኬት አልባ ከሆነ ደግሞ መጅሊስን አዳክሞና ገሸሽ ተደርጎ መጅሊስ የእርስ በርስ የሽኩቻ ሜዳ ሲሆን ይሄኛው ራሱን የቻለ ሌላ ድርጅት ሆኖ በመቀጠል “የኡለማ ድርጅት ነው”፣ “ዳዕዋ በማስፋፋት”፣ “ዲን በማስፋፋት የፈለጉትን ይሠራል ስለዚህኛው ምን አገባቸሁ” በሚል ዓይነት አካሄድ ዘላቂነታቸውን ለማረጋገጥ መሠል ዘዴዎችን ከወዲሁ ለመቀየስ ሞክረዋል፡፡
ጧት ላይ የተደረገው ስብሰባ ይህን የመሰለ ይዘት የነበረው ሲሆን ተሰብሳቢዎቹ 50 50 ብር አበል ወስደው ተመልሰዋል፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 15, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: