RSS

22ኛው ሣምንት የተቃውሞ ድምፅ በአወሊያ!

07 Apr

22ኛው ሣምንት የተቃውሞ ድምፅ በአወሊያ!

ሰኔ 1 2004

( part 1)
ህዝበ ሙስሊሙን ለ15ኛ ሣምንት በአወሊያ ያሰባሰበው የዛሬው የሰኔ 1 2004 የተቃውሞ ውሎ በደማቅ ሁኔታ ተካሄዶ ዋለ፡፡ ጁምዓ ሶላት ሰባት ሰዓት ላይ መጠናቀቁን ተከትሎ እስከ ስምንት ተኩል ድረስ ቆይታ ያደረገው ይኸው ትዕይንተ ህዝብ በተለያዩ የመድረክ ዝግጅቶች ደምቆ ውሏል፡፡ ውሏችን ፍፁም ሠላማዊ መሆኑን በማስገንዘብ ደረጃ ምናልባትም ልዩ ተልዕኮ በመያዝ ሰርገው የገቡ አካላት ካሉ ታዳሚው ህዝብ እንደተለመደው ሰላሙን እንዲጠብቅ ጠንካራ ይዘት ያለው መልዕክት በተደጋጋሚ መነገሩ የዕለቱን ውሎ መጀመር ያበሰረ ነበረ፡፡ የመድረኩን ፕሮግራሞች በመከተል የአንድነታችን መገለጫ የሆነው እጅ ለእጅ በመያያዝ ለበርካታ ጊዜ በተደጋጋሚ የተክቢራ ድምፆች አስተጋበተዋል፡፡
የሳምንቱን የኮሚቴውን ውሎ በማስመልከት ወደ መድረክ የቀረበው አቡበክር አህመድ ከወትሮ ለየት ያሉ እና ጠንካራ ይዘት ያላቸውን አሳሳቢ መልዕክቶችን በማከል ውሏቸውን አቅርቧል፡፡ ከዚህ በማስቀደም እንደ ኮሚቴ ይደረጋል እየተባለ የሚወራውን ምርጫ በማስመልከት ሁሉም ህዝበ ሙስሊም በያለበት በየመስጂዱና ሌሎች አመች መንገዶች እያደረገ ያለውን ውይይት በማድነቅ ይኸው አካሄድ እስካሁን የተሄደው መንገድ ውጤቱ እንዳይበላሽ እና ምርጫው በተገቢው መልኩ እንዲካሄድ በማድረግ ረገድ የማይተካ ሚና ስለሚጫወት በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የጠበቀ አደራውን አስተላልፏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ከውይይት በኋላ ያሳለፏቸውን ውሳኔዎች ኮሚቴው የሰማቸው መሆኑን ገልጦ ይህ በራሱ ህዝቡ ምንም እንኳ ወኪል በማለት ኮሚቴ ቢመርጥም የጉዳዩ ባለቤት ራሱ መሆኑን እና ለራሱ ራሱ እንደሚውቅ ያስመሰከረበት አጋጣሚ እንደሆነ ገልጧል፡፡
ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ የኮሚቴ ውሎ ሲል ባካተተው ንግግሩ በአሁኑ ሰዓት በመንግስት እና “ወርዷል” እየተባለ በሚነገርለት መጅሊስ አማካይነት እየተደረጉ ያሉትን አሳዘኝ ሂደቶች በመንተራስ ህዝቡ ሊወስድ የሚገባውን እርምጃ ከወዲሁ እንዲያስብበት የቤት ስራ ሰጥቷል፡፡ በዚህም ከዚህ በኋላ የሚመጣው ነገር ለማንም ግልፅ ባለመሆኑ ምክንያት በብዙ ልፋት የህዝብ አደራ በመሻከም የህዝቡን ጥያቄ እዚህ ደረጃ ያደረሰው የኮሚቴ ስብስብ አደጋ ቢደርስበት ሠላማዊ ትግሉ መቋረጥ የለበትም እና የህዝቡን አደራ መሸከም የሚችሉ ተተኪ የሕዝብ ተወካዮች (ኮሚቴዎች) ህዝቡ እንዲያዘጋጅና በቀጣዩ መድረክ ይዞ እንዲቀርብ አሳስቧል፡፡ “ኢንሻ አላህ!” የሚለው ድምፅ ከመድረክ በስተጀርባ ማስተጋባቱ ከኮሚቴው በስተጀርባ የተሰለፈው የህዝብ ደጀን በኮሚቴው ላይ ቀርቶ በሌሎች አካላት ላይም አደጋ ቢደርስ ትግሉ እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ መቀጠሉን ያረጋገጠ ነበር፡፡ ኮሚቴው የህዝብ ተወካይ፣ የህዝብን ድምፅ ወደ መንግስት የሚያደርስ የመንግስትን ምላሽ ለህዝብ የሚያደርስ አካልና በህዝብ የተመረጠ እንጂ ከህዝብ በስተጀርባ ተደብቆ የራሱን አጀንዳ ለማስፈጸም ራሱን የሾመ አካል እንዳልሆነ ያረጋገጠው ኡስታዝ አቡበክር አህመድ በመንግስት አካላት የተያዘውና በተደጋጋሚ በመገናኛ ብዙሃን እየተነዛ ያለው የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በህዝብ ዘንድ ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው እንዲሁም በዚህ ተግባር ህዝብ የጣለባቸውን አደራ ዳር ለማድረስ የሚሄዱበትን አካሄድ እንደማያሰናክለው በድጋሜ አረጋግጧል፡፡ ለዚህም ንግግሩ ከፍተኛ የተክቢራ ድምፅ ምላሽ ከህዝቡ ተችሮታል፡፡ ይሁንና በቀጣይ የሚመጣው ስለማይታወቅ ሁሉም ሙስሊም ህብረተሰብ በሚኖርበት አካባቢው እንደተለመደው ስለቀጣዩ የተቃውሞ እጣ ፋንታ አካሄድና ስለ ተተኪ የኮሚቴ አባላት ውይይት እንዲያደርግና ውጤቱንም ከዚህ ቀደም በነበረው መንገድ በቀጣዩ የጁምዓ መድረክ ይዞ እንዲመጣ አደራውን አስተላልፏል፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 7, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: