RSS

22ኛው ሣምንት የተቃውሞ ድምፅ በአወሊያ!

07 Apr

22ኛው ሣምንት የተቃውሞ ድምፅ በአወሊያ!

ሰኔ 1 2004

( part 2 )

ምርጫን በማስመልከት ከህዝብ የተሰወረ ስራ ውስጥ ለውስጥ እየተሰራ መሆኑን እና ከዚህ ጋር በተያያዘ ህዝቡ የማያውቀው “መተዳደሪያ ደንብ” ተዘጋጅቶ ምርጫው በዚያ መሠረት ሊካሄድ ዝግጅቱ መጠናቀቁን ያጋለጠው ንግግር የተሰማው ደግሞ ከሌላኛው የኮሚቴ አባል አሕመዲን ጀበል ነበር፡፡ አሕመዲን ጀበል እንደተለመደው በእጁ የሚገኙትን ተጨባጭ መረጃዎችን ተንተርሶ ህዝቡን ያስደመመና በሐዘን ስሜት ያስዋጠ ከመጋረጃ በስተጀርባ የሚደረጉትን ህገ ወጥ ስራዎች አብራርቷል፡፡ “ምርጫ የሚመስል ድራማ እየተሠራ ነው” ያለው አሕመዲን ጀበል ለዚህ ማስረጃ ይሆናሉ ያላቸውን መረጃዎች ይፋ አውጥቷል፡፡ ለምሳሌ ያክል በኦሮሚያ ክልል እና በአዲስ አበባ ከተማ ይኸው ስራ እየተጧጧፈ ያለ መሆኑን ያስረዳው አሕመዲን ባለፈው ቅዳሜ የተጠናቀቀውን የአህባሽ ስልጠና ተከትሎ በኦሮሞያ አምስት (ስማቸው ተነስቷል) ሰዎች ምርጫውን ለማስፈፀም በሚል ከህዝብ እውቅና ውጭ ተመልምለው ቅዳሜ እሑድና ሰኞ አዳማ ላይ ተጨማሪ ስልጠና እንደሚሰጣቸው ያገኘውን መረጃ ለህዝቡ ይፋ አድርጓል፡፡ በአዲስ አበባም ቢሆን እኛ እዚህ ተቃውሟችንን ለማሰማት በተሰበሰብንበት ቅፅበት (ስምንት ሠዓት አካባቢ) ምርጫውን እንዴት ማስኬድ እንዳለባቸው ለመምከር መጅሊሶች ቶታል አካባቢ በሚገኘው የአህባሾች ማዕከል ውስጥ ለስብሰባ መቀመጣቸውን አጋልጧል፡፡ ይህ ሁሉ የህዝብን ድምፅ መጨፍለቅና መናቅ ነው ያለው ተናጋሪው ህዝቡ ከዚህ በኋላ ያለውን ሂደት በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲጠብቀውና ከመሰል አወናባጅ ተግባራት ራሱን፣ቤተሰቡን እና በቅርብ የሚያውቀውን በሙሉ እንዲጠብቅ፣ እንዲወያይ እና እንዲከላከል አደራውን አስተላልፏል፡፡ ከመተዳደሪያ ደንብ ጋር በተያያዘ ያነሳቸው ነጥቦች በህዝቡ ዘንድ አሳሳቢ የሆነ ነበር፡፡ ወርደዋል የተባሉት የመጅሊሱ አመራሮች በተለይም አሕመዲን አብዱላሂ ጨሎ እና ምክትሉ አቶ አዛም ዩሱፍ ምርጫውን አስመልክቶ ከ ዶ/ር ሽፈራው ጋር ውይይት እንዳደረጉ የደረሰው መረጃ ዲመለክት “ወርደዋል” መባሉ ምኑ ላይ እንደሆነ አግራሞቱን ለህዝቡ አካፍሏል፡፡ የመጅሊሱን መተዳደሪያ ደንብ እንዳሻቸው የሚያሻሽሉት እነኚሁ አካላት ዛሬ ደግሞ ጉድ ይዘውልን ብቅ ብለዋል ሲል የተደረገውን ለውጥ አጋልጧል፡፡ በዚሁ ተሻሻለ በተባለው መተዳሪያ ደንብ መሠረት ምርጫውን በማሸነፍ በድጋሜ የመጅሊስን ወንበር ለመቆናጠጥ እየሮጡ ሲሆን ምርጫውን እንደሚያሸንፉ በመተማመናቸው የህዝብን ድምጽ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማፈን የሙስሊሞችን ተቋም እንደልብ መፈንጨት ያስችላቸው ዘንድ አንድ “ተመራጭ” የምክርቤት አባል በድጋሜ ለምርጫ ከመቅረቡ በስተፊት ቀድሞ የነበረው የ አምስት አመት የቆይታ ዕድሜን ወደ አስር ዓመት እንዲያድግ በማድረግ መተዳደሪያ ደንቡን እንዳሻሻሉት ይፋ አድርጓል፡፡ ይህም በአዲሱ መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 42 ንዑስ አንቀፅ 1 ላይ እንደሚገኝ ያሳወቀው ተናጋሪው ከአስር ዓመት የስልጣን ቆይታ በኋላም ቢሆን እንደ አስፈላጊነቱ የስልጣን ዕድሜው ሊራዘም እንደሚችል ጨምሮ አስረድቷል፡፡ ይህ ምን ማለት እንደሆነ የጠየቀው አሕመዲን ጀበል ሕዝብን ከመናቅ እና “ጌታዋን የተማመነች…” ከሚለው የተለየ እንዳለሆነ በህዝብ የአግራሞት ድምጽ ታጅቦ ስሜቱን ገልጧል፡፡ ይኸው የህዝቡን ድምጽ የማኮላሸት እንቅስቃሴያቸው አካል እንደሆነ የተጠቀሰው ሌላኛው ነጥብ በምርጫው ውስጥ የተሳተፉና እነሱ የማይፈልጓቸው አካላት ቢመረጡ እንኳን ሊወሰድ የታቀደውን እርምጃ ያጋለጠበት መረጃ ይገኛል፡፡ በ አዲስ አበባ ስራ አመራር ኮሌጅ ለሦስት መቶ ሰዎች በተሰጠው ስልጠና ላይ የተገኘው የዑለማ ምክር ቤት ምክትል ጸሀፊ ኢዘዲን እንደተናገረው ምርጫውን በዚህ መልኩ ተቆጣጥረነው ከወረዳ ሾልከው ቢመጡ እንኳን ክ/ከተማ ላይ እናስወጣቸዋል፣ ከዚያ ቢያልፉ ደግሞ ዞን ላይ፣ ከዞን ቢያልፉ ክልል ላይ እስከ ፌዴራል ድረስ መንጥረን እናስወጣቸዋለን ማለቱ ተሰምቷል በማለት ይህንኑ በመረጃ የተደገፈ ንግግሩን ለህዝብ አስደምጧል፡፡
ምርጫ በቀበሌ አሊያም በመስጂድ መሆኑ ያለውን ጥቅምና ጉዳት በሰፊው ያብራራ ሲሆን ህዝቡም ይህንን ሁኔታ ተገንዝቦ ሲያበቃ በየአካባቢው እያደረገ ያለው ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስቧል፡፡
በመጨረሻም አሁን ያለንበት ወቅት እስከ አሁን ከተጓዝንበት ሁሉ እጅግ አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን ተገንዝበን እስካሁን ከወሰድነው ጥንቃቄ በላይ በመውሰድ እዚህ ደረጃ ያደረስነውን ትግላችንን ፍሬ ለመልቀም መሰናዳት እንደሚኖርብን እና ለተንኮለኞች ምንም ዓይነት በር መክፈት እንደማይኖርብን የጠነከረ አደራውን አስተላልፏል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል ኡስታዝ አቡበክር አሕመድ ያስተላለፈውን መልዕክት ህብረተሰቡ አፅንኦት እንደሚሰጥበትና በቀጣዩ ሳምንት ሲመጣ ምለሹን ይዞ እንደሚመጣ ያለውን ተስፋ ገልጧል፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 7, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: