RSS

ድምፃችን ይሠማ! (ከደሴ)

07 Apr

ድምፃችን ይሠማ!
(ከደሴ)

በደሴ ከተማ የሚካሄደው የአንድነትና የሶደቃ ፕሮግራም ዝግጅት ተጧጡፏል
(ሰኔ 11 2004 ከቀኑ 10፡00 በኋላ)

በነገው ዕለት ማለትም ማክሰኞ ሰኔ 12 2004 ደሴ በፉርቃን አደባባይ ከ 50,000 በላይ ታዳሚ ይሳተፍበታል ተብሎ የሚጠበቀው ታላቅና ታሪካዊ የአንድነትና የሶደቃ ፕሮግራም ይደረጋል፡፡ የዚህ ዝግጅት ዓላማ በሙስሊሙ ሕብረተሰብ ላይ የመጣው በላዕ አላህ ሱብሐነሁ ወተዓላ እንዲመልሰውና በአሁኑ ሰዓት የተፈጠረውን አንድነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሆነ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፕሮግራሙ አዘጋጅ ገልጠዋል፡፡ አላማጣ፣ ቆቦ፣ ወልዲያ፣ መርሣ፣ ሀርቡ፣ ደጋን፣ ገርባ፣ ከሚሴ፣ ኮምቦልቻ፣ አዲስ አበባ፣ ወግዲ፣ ወይራምባ እና መካነሠላም የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ይመጡባቸዋል ተብለው የተነገሩ ዋና ዋና አካባቢዎች ናቸው፡፡ በዚህ ዘግጅት ላይ የደሴ ከተማ መስጊድ ኢማሞች በሙሉ እንደሚሳተፉ የታወቀ ሲሆን ሸኽ ሙሐመድ ጌታ፣ የመንዙማ አቀንቃኙ ሙሐመድ አወል ሐምዛ፣የታሪክ ምሁራን እና ዱዓቶችም ጥሪ እንደተደረገላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሙስሊሙ ህዝበ ተወካዮች አህመዲን ጀበልና ካሚል ሸምሱም ተካፋይ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በተለይም የደሴ አካባቢ ሙስሊም ህብረተሰብ ያነሳውን ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄ በትክክል ለማስገንዘብ መልካም አጋጣሚ ሊፈጥር እንደሚችል የተናገሩት አዘጋጅ አካላት ይህንን ፕሮግራም ከጅምሩ ለማኮላሸት ጥረቶች መደረጋቸው ይበልጥ እንዳበረታታቸው ገልጠዋል፡፡ ለምሳሌ ያክል ህዝቡ እርስ በርሱ ጥሪ በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት ዝግጅቱን ያዘጋጁት አክራሪዎችና ወሐቢያዎች ናቸው እንዳትሄዱ ከማለት ጀምሮ ለዕለቱ የሶደቃ ዝግጅት ፍጆታ ይውል ዘንድ በማህበር ተደራጅተው እንጀራ የሚጋገሩት ግለሰቦች ተስማምተው ቀብድ ከተከፈላቸው በኋላ የቀበሌ 20 አመራር አቶ ብርሐኑ እንደከለከሏቸው፣ ማኅበርተኞችም የከፈላችሁንን ቀብድ ዱቄት ገዝተንበታል እሱን መውሰድ ትችላላችሁ መባላቸው በምሳሌነት የጠቀሷቸው እንቅፋቶች ናቸው፡፡ የእንጀራ አቅርቦት ዝግጅት መስተጓጎል ችግሩን ህብረተሰቡ ከሰማ በኋላ ሁሉም በግሉ የራሱን ጥረት በመጠቀም የሚጋግረውም እየጋገረ፣ የሚገዛውም እየገዛ የእንጀራ አቅርቦት ክፍተትን ለመሙላት እንጀራ በማጋዝ ላይ መገኘታቸውን ለማየት ተችሏል፡፡ አዘጋጅ ክፍሉም ይህን ክፍተት ለመሙላት በማሰብ የሩዝ ፍጆታ መጠኑን ወደ 20 ኩንታል ከፍ እንዳደረገው ገልጧል፡፡
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተሳታፊ ይታደምበታል ተብሎ ከመጠበቁ ጋር በተያያዘ አዘጋጆቹና አስተባባሪዎቹ በከፍተኛ መነቃቃት ከላይ ታች ሲሮጡ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ በአካል በመገኘት ያስተዋለ ሲሆን (ከዚህ ጋር የተያያዙ የናሙና ስዕሎችን እና ቪዲዮችን ይመልከቱ) ይህ ፅሁፍ እስከተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ የ20 በሬወች እና የ13 ሙክት ፍየሎች እርድ ተከናውኗል፡፡
በነገው ዕለት በድምቀት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ይኸው የአንድነትና የሶደቃ ዝግጅት ውሎን አስመልክቶ ድምፃችን ይሰማ ሪፖርቷን ታደርሳችኋለች፡፡ኢንሻ አላህ፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 7, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: