RSS

ደማቅ የ አንድነት እና የሶደቃ ዝግጅት በቄራ ሠላም መስጂድ ተካሄደ!

07 Apr

ደማቅ የ አንድነት እና የሶደቃ ዝግጅት በቄራ ሠላም መስጂድ ተካሄደ!

ከሁለት ወራት በፊት በአንሷር መስጂድ (አየር ጤና) የተጀመረው እና የሙስሊሙን ኅብረተሰብ አንድነት ለማጠናከርና የመጣውን በላእ አላህ እንዲመልሰው በማሰብ የአንድነት እና የሶደቃ ዝግጅት በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ የክልል ከተሞች ከጥቂት ወራት ወዲህ በስፋት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የዚሁ አካል የሆነውና በትላንትናው ዕለት እሁድ ሰኔ 3 2004 የአገራችን ታላላቅ ዑለሞችን ጨምሮ በርካታ ታዳሚ በተገኙበት የደመቀ ዝግጅት ተካሂዶ ውሏል፡፡

የዕለቱ ፕሮግራም ከጧቱ ሦስት ሠዓት እስከ ስምንት ሠዓት ቆይታ የነበረው ሲሆን ክርስትያን ወንድሞችም የፕሮግራሙ ተሳታፊዎች የነበሩ መሆናቸው ዝግጅቱ ልዩ ገፅታ እንዲላበስ አስችሎታል፡፡

የዕለቱ ውሎ በዛ ያሉ የመድረክ ዝግጅቶችን ያቀረበ ሲሆን ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል፣ ዶ/ር ጄይላን፣ ሼኽ ሠይድ (የሱመያ መስጂድ ኻጢብ) በመድረኩ ላይ ንግግር ካደረጉ መካከል ይገኙበታል፡፡

የኮሚቴው አባል ካሚል ሸምሱ በዕለቱ ባደረገው ንግግር ሙስሊሙ ዜጋ ፍፁም ሠላማዊ መንገድን በመከተልና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በማክበር እየጠየቀ ያለው ሐይማኖታዊ የመብት ጥያቄ ከአምስት ወራት በላይ ማስቆጠሩን አስታውሶ ይህን ያክል ወራት ያስቆጠረው አካሄድ በጥያቄዎቹ ይዘት ላይ ያስከተለው ለውጥ እንደሌለ በመጠቆም ጥያቄዎቹን ከጥቂት ማብራሪያዎቻቸው ጋር በማያያዝ ህጋዊነታቸውንና ፍፁም ሐይማኖታዊነታቸውን በድጋሜ አስታውሷል፡፡

ሌላው የኮሚቴው አባልና ሰብሳቢ አቡበክር አሕመድ ወደ ዝግጅቱ መቋጫ አካባቢ ባደረገው ንግግር በመድረኩ ላይ እና ከመድረኩ ውጭ የሰፊውን ሙስሊም ኅብረተሰብ የመብት ጥያቄ ሒደት በትክክሉ ባለመረዳታቸው ምክንያት የተፈጠረ ብዥታ አለ በማለት እስካሁን የነበረውን ሂደት ግልፅ አድረጓል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሙስሊሙን አደራ ተሸክሞ ሌት ቀን በመልፋት ላይ ያለው እና አስራ ሰባት አባላትን ያቀፈው ኮሚቴ “ስልጣን ፈላጊ ነው” እንዲሁም አወሊያ የሚሰባሰቡት “ስልጣን ፈላጊዎች ናቸው” የሚባለውን አሉባልታ ያለውን ተጨባጭ እውነታ ከመሠረቱ በማብራራት እና በተለይም ኮሚቴው አብዛኛው አባላቱ በሌሉበት መመረጣቸውን ጠቁሞ ኮሚቴው ይህን የህዝብ አደራ ህዝብ እንደሚፈልገው ዳር ካደረሰ በኋላ ሁሉም ወደ ስራው እንደሚመለስ እና ማንኛውም የኮሚቴ አባላት የመመረጥም ሆነ ስልጣን የመያዝ ፍላጎት የላቸውም፣ ይኸውም በሂደት በተግባር የሚታይ መሆኑን ማየት ይቻላል ያለው አቡበክር ይህ ስለተወራ ብቻ ህዝብ ከሰጠን ኃላፊነት መቼም ወደ ኋላ አንልም በማለት የአሉባልታውን መሠረተ-ቢስነት አሳይቷል፡፡ ይህም በህዝቡ ዘንድ በደማቅ ተክቢራ መታጀቡ ተስተውሏል፡፡

በዕለቱ ዝግጅት ትኩረት ተሰጥቶት ከዋሉት ነጥቦች መካከል የመጅሊስ ምርጫ ይገኝበታል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ምርጫን አስመልክቶ በመንግስት እየተደረጉ ናቸው በሚል የሚናፈሱት ወሬዎች እውነታ ካላቸው ምርጫው ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው ተነግሯል፡፡ ምርጫ ይደረጋል የሚለው ምላሽ የመነጨው የሙስሊሙን ዜጋ ጥያቄ ተንተርሶ መሆኑ ግልፅ መሆኑ እየታወቀ አሁን ከህዝብ በተሰወረ አኳኋን እየተደረገ ያለው ነገር ሙስሊሙን እና ያነሳውን ጥያቄ የማይወክል መሆኑን የሚያስረዱ አስተያየቶች ተደምጠዋል፡፡ ምርጫ ከተባለ የምርጫን መሠረታዊ መሥፈርቶች ማሟላት እንደሚገባው አፅንኦት ሰጥተው የተናገሩት የመደረክ ተናጋሪዎቹ ሙስሊሙ ኅብረተተሰብ እየተደረገ ያለውን ነገር ትኩረት ሰጥቶ እንዲከታተለውና ሂደቱ የህዝቡን የልብ ትርታ በትክክል ማድመጥ እስካልቻለ ድረስ በሠላማዊ ሂደት ትግላቸውን እንዲቀጥሉ አደራቸው አስተላልፈዋል፡፡

የህፃናቱ የአንድነታችን መገለጫ የህብረት ነሺዳ እና የገጣሚ ሙኒር ግጥም የእለቱን የመድረክ ቆይታ ለዛ እንዲኖረው ሲያደርጉ በሠላማዊ የመብት ጥየቃ ሂደትም ሆነ በሁለንተናዊ ዘርፍ ሙስሊሙን ያማከለ ስራ ለሰሩ አካላት መድረኩ ያዘጋጀው ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 7, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: