RSS

ድምፃችን ይሰማ ፔጅ የሙስሊሙን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሁለንተናዊ መረጃዎችን ለኡማው የምናቀብልበት መስኮት በመሆን እያገለገልች ትገኛለች፡፡ አላህ ያበርታት

06 Apr

ድምፃችን ይሰማ ፔጅ የሙስሊሙን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሁለንተናዊ መረጃዎችን ለኡማው የምናቀብልበት መስኮት በመሆን እያገለገልች ትገኛለች፡፡ አላህ ያበርታት፡፡

ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ከህዝብ ለህዝም የሚተላለፉት መልዕክቶች በጫር ጊዜ ውስጥ እንደሚሠራጭ ሁሉ ለአሁኑም ከትላንትናው የአወሊያ ውሎ ጋር በተያያዘ የሚከተለውን መልዕክት በማዳረስ ትላንት እጅ ልእጅ ተያይዘን የገባነውን ቃል በመተግበር እንሽቀዳደም::

በነገው ዕለት የኢሕአዴግ ሙስሊም አባላት ስብሰባ እንዳላቸው ታውቋል፡፡ የስብሰባው ዓላማ አባላቶቹን በመጅሊስ ምርጫ (ምርጫ ለማድረግ አስበናል) እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በማወያየት ያቀደውን መተግበር እንዲያስችለው ድጋፉን እንዲሰጡት ለመጠየቅ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ከዚህ ቀደም ሙስሊም የኢሕአዴግ አባላት ባደረጓቸው ስብሰባዎች በሙሉ ተሰብሳቢዎች መድረኩን ቻሌንጅ ማድረጋቸው ለኢሕአዴግ የራስ ምታት ሲሆንበት ለዚህ ምክንያት ይሆናሉ ያላቸውን እና አሁንም ቻሌንጅ ያደርጉናል ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች ባለቀ ሰዓት በስልክ እንዲጠሩ ተደርጓል፡፡
ነፃ ምርጫ የምንለው እና የምንቀበለው ምርጫ ምን ምን መስፈርቶችን ሲያሟላ ነው የሚለውን ህዝቡ ትላንትና በአወሊያ የተነገረውን በማስታወስ መረጃውን መለዋወጥ ይኖርበታል፡፡

1. ነፃና ገለልተኛ አካል የሚያካሂደው መሆን አለበት፡፡
ምርጫውን “ገለልተኛ” ነው የተባለው የዑለማ ምክር ቤት ገለልተኛ አካል አይደለም፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው የዑለማ ምክር ቤቱ መጅሊስን ደግፎ በተደጋጋሚ መግለጫ መስጠቱ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ እንደዚህ ከሆነ ታዲያ በምን አካል ነው ምርጫ የሚካሄደው? ያለ ተቋም ሜዳ ላይ ማድረግ አንችልም ብሎ መንግስት ቢጠይቅ መልሱ ቀላል ነው፡፡ የምርጫውን ተዓማኒነት ለማስጠበቅ ከተፈለገ ከየመስጂዱ ኢማሞችን፣ ታዋቂ ሰዎችን ሁኔታውን እንዲያመቻቹና ምርጫውን ገለልተኛ ሆነው እንዲያስፈፅሙ ማድረግ ይቻላል፡፡
2. የምርጫ አፈፃፀም መመሪያው እና ሂደቱ ለህዝብ ይፋ ሆኖ ህዝቡ ስለሚደረገው
ምርጫ ግንዛቤ መያዝ አለበት፡፡
3. ምርጫ የሚደረገው የት ነው?

ዘግይቶ በደረሰን መረጃ መሠረት የቀበሌ መዋቅር ፈርሶ ወደ ወረዳ በመቀየሩ ምክንያት ምርጫ በወረዳ ይካሄዳል፡፡ ይሁንና ምርጫ በወረዳ ከሆነ በቀበሌ ሊደረግ ከታሰበው የባሰ ችግር እንደሚፈጠር ይታወቃል፡፡ ከሌላ ወረዳ መጥቶ ቢመረጥ፣ ቢመርጥ፣ መታወቂያ ስላለው ብቻ ለገንዘብ ያደረ ካድሬ እመርጣለሁ ቢል ወዘተ ቢከሰት መከላከያው ምንድን ነው?
4. ምርጫ ቀኑ መች ነው? የ92ቱ ምርጫ እንኳን የምርጫ ቀኑ ቀደም ብሎ በይፋ መታወጁ ይታወሳል፣ መጅሊስ እና ቢሮዎቹ ተሸገውም ቢሆን ምርጫው ተጭበርብሮ ነው ያለፈው፡፡ የአሁኑ በይፋ አንድ ወር እንኳን ጊዜ ባልተሰጠበት እና በሚስጥር ተይዞ ምርጫው እንዴት ተዓማኒነት ይኖረዋል? ይህ ምርጫ አይደለም፡፡
5. ድምፅ የሚሰጠው እንዴት ነው? በካርድ ነው? በድምፅ ቆጠራ ነው? ተመራጩስ ማን ነው? የተመራጩን መስፈርት የሚያወጣው ማን ነው? ስልጠና የወሰደ/ያልወሰደ?
አሁን በተያዘው አረዳድ ሙስሊሙ ሕገ መንግስቱን ስለማያውቅ የአሁኑን ስልጠና የወሰደ አገሪቱ ያለችበትን ተጨባጭ ይበልጥ ስለሚያውቅ መመረጥ ያለበት እንዲህ ዓይነት ሰው ነው የሚል አድሏዊነት የተጠናወተው አካሄድ ግልጽ እየሆነ መጥቷል፡፡ ይህ ህዝበ ሙስሊሙን መናቅ ነው፡፡ በአንድ በኩል ሕገ መንግስቱን አታውቁም በሌላ መልኩ ደግሞ የተዋህዶ ቤተክርስትያን ምርጫ ሲያደርግ ህገ ምንግስቱት የሚያውቅ ኮርስ የወሰደ የሚባል ነገር እንደሌለ እየታወቀ ፌዴራል ጉዳዮችም
6. ምርጫው ተጭበረበረ ቢባል እንዴት ነው የሚጣራው? ታዛቢውስ ማን ነው? ምርጫው ኢስላማዊና ዲሞክራሲያዊ ነው ወይስ ከነዚህ ያፈነገጠ?
አሁን እየተደረገ ያለው ነገር ሙስሊሙን “ነባር” እና “አዲስ” ብሎ በመከፋፈል የሚመረጡትም ሆነ የሚመርጡት “ነባሮቹ” ብቻ ናቸው በሚል የእርስ በርስ ግጭቱን ለማጦዝ ተነስተዋል፡፡ ይህንንም በተመለከተ የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ አቶ ፀጋዬ በርሔ እና ዶ/ር ሽፈራው ግልፅ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ ምርጫው በዚህ መልኩ ነው መካሄድ ያለበት የሚለውን ትዕዛዝ ባስተላለፉበት ወቅት የመጅሊሱ ዋና ፀሐፊ “ነባር” እና “አዲስ” ብለን ከፋፍለን ምርጫ ብናደርግ የባሰ ችግር አይፈጠርም ወይ? ብለው ቢጠይቁ “እኛ ለዚህ ተዘጋጅተናል እናንተን አያገባችሁም!” በማለት ዶ/ር ሽፈራው ተናግሯል፡፡ ሁኔታው በዚህ መልኩ እንዲቀጥል ከተደረገ ነገም ወደ ተቃውሞ ወደ አደባባይ ሙስሊሙ የማይወጣ ምንም ዓይነት ምክንያት አይኖርም፡፡ በኢሕአዴግና በሙስሊሙ መካከል ሙሉ በሙሉ የመቆራረጥ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
ከዚህ በላይ ያሰፈርናቸውን አንኳር ነጥቦች ልብ በማለት ህዝበ ሙስሊሙ እርስ በርስ ተነጋግረሮ ሲያበቃ ያገኘውን አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም መረጃዎችን ለመቀባበል ትላንት ጁምዓ በአወሊያ እጅ ለእጅ ተያይዘን የገባነውን ቃል በማክበር ተግባራዊ ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ይህን ያክል ርቀት የተጓዘውን ሠላማዊ ትግል መጠበቅ የምናስችለው ተስፋ ባለመቁረጥ እያንዳንዷን እርምጃችንን በጥንቃቄ መራመድ ይኖርብናል፡፡ ለዚህም ይረዳን ዘንድ ሁሉም ሙስሊም ልክ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርገው ሁሉ ስልክ በመደዋወልም ሆነ ሜሴጅ በመላላክ ነገ በሚደረገው ስብሰባ ላይ የሚሳተፉትን ሙስሊም የኢሕአዴግ አባላት ሙሉ መረጃ ማቀበል ይኖርብናል፡፡ የስብሰባው ታዳሚዎችም ከዚህ ቀደሙ የነበራቸውን የነቃ ተሳትፎ በመድገም ለፍትህና ለሀቅ የቆሙ መሆናቸውን ማስመስከር እንደሚጠበቅባቸው ልንነግራቸው ሊያውቁትም ይገባል፡፡ ተሳታፊዎች ምርጫን በተመለከተ በሚደረገው ውይይታቸው ወቅት ስለ ምርጫ እና ስለተመራጮች ማንነት ግልጽ መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚጠበቅባቸውና የሚመረጡ ሰዎች ሙስሊም መሆን እንዳለባቸው፣ በሙስሊሙ ዜጋ በውል የሚታወቁ መሆን እንዳለባቸው ጠንከር ባለ መልኩ መልዕክት ማስተላለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በዚህ ረገድ ሁሉም ሙስሊም ሌሊቱን ሙሉ አጭር መልዕክት ያዘለ ሜሴጅ በመለዋወጥ የበኩላችንን እንወጣ፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 6, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: