RSS

ዜና ጎንደር

06 Apr

ዜና ጎንደር
አሰላም ዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ
በትላትናው ዘገባየ ዛሬ ማለትም ሚያዚያ 19/2004 በጎንደር ከተማ የአህባሽ የማጥመቂያ ስልጠና እንደሚጀምር መጥቀሴ አይዘነጋም፡፡ታዲያ በገባሁት ቃል መሰረት የዛሬውን እንደሚከተለው አቀርበቀለሁ፡፡
ከቀኑ ጁምዓ 6፡00 ሰዓት፤የጎንደር ከተማሙስሊም ህብረተሰብ እንደተለመደው የጁመዓ ሰላትን ለመስገድ ከድሮው በተለየ መልኩ በጎንደር ከተማ ወደሚገኘው ጃምዕ አልከቢርመስጊድ በሰልፍ ይነጉዳል፡፡ድባቡ የሆነ ነገር እንዳለ ያመላክታል፡፡እኔም ከሚተመው ሙስሊም አንዱ ነበርኩ፡፡ ገብተንቁጭ ከማለታችን በጎንደሩ የአህባሽ “ሸህ”ሙስጦፋ አሚኑ ፊታውራሪነት የሚመራው ቡድንሁለት ነጫጭባ ሊባኖሳውያን የአህባሽ ዳዒዎችን ይዞ ወደ ሚመምበሩ አመራ፡፡ መስጊድ ውስጥ የነበሩት ሙስሊሞችም በአግራሞት ይመለከቷቸው ነበር፡፡ ኢስላዊ ሰላምታ ከሰጡና ከተቀመጡ በኋላ የተለመደ የቅጥፈት ዳዕዋቸውን ያንቆረቁሩት ጀመር፡፡ የነርሱን መግባት የተመለከተው ሙስሊምም በሞባይልና በስልክ በመጠራራት በደቂቃዎች መስጊዱ ሞላ፡፡ ስለ “ውሀብያ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የማስፈራሪያ ጭራቃዊ ምስል” ትረካቸውን ቀጠሉ፡፡ ሊባኖሳዊው ነጭ ዳዒ ሲናገር የኛው “ለሆዱ አዳሪ” ትርጉም ነው ያለውን ማነብነብ ጀመረ፡፡ አጂብ የሚያሰኝ ነገሮች ቀረቡ፡፡ ስለ የአላህ ሲፈት፣ስለ ሀላል ቢድዓዎች ስላሏቸው፣ስለ ተወሱል፣ስለ ተበሩክ እና ተያያዥነት ስላላቸው ጉዳዮች የተምታቱ ለታዳሚውም ግልጽ ያልሆኑ መረጃዎችን አቀረቡ፡፡ ተዋዶና ተፋቅሮ የኖረውን የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብ ግራ በማጋባትበነዚህ ርዕሶች ዙሪያ ለ5 ቀናት ስልጠና ስለሚሰጥ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መሳተፍ እንደሚችልና ሊባኖሳዊው ነጭ ዳዒ “ኢርሀቢውሀቢያ” ወይም አሸባሪ ውሀብያ ያሏቸውን እንደሚያስለቅሱ ዛቱ፡፡ ከአዲስ አበባ ነጩን የአህባሽ ዳዒ አጅበው ከመጡት ውስጥም አንደኛው “ውሀብም መጥታ ጉዷን መስማት ትችላለች” በማለት በትዕቢት ሲናገር ወጣቶች መስጊድ ውስጥ ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ የፖለቲካ ሥራ ነው እንዴ የተያዘው በማለት ሁሉም ተበሳጨ፡፡ ድባቡምተቀየረ፡፡በወጣቶች የተዘጋጁና በሽዎች የሚቆጠሩ የመጅሊሱ ፕረዚደንት ተብየውና የአህባሽ ቀኝ እጅ የሆነው እስራኤላዊው የጥመት ፕሮፌሰር ሀጋይ የአህባሽን አስተሳሰብን እንዴት ማስረጽ እንዳለባቸው ያዘጋጁትን ጥናት ሲያስረክቧቸው የሚያሳይ ምስልና ስለዚሁ የሚያስረዳ በራሪ ወረቀቶችሲበተኑ ውለዋል፡፡
ከተበተኑት መረጃዎችም ውስጥ ጥቂቶቹ፡-
1. እኛ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ አንድነታችን ጠብቀን ዲናችንን በመተግበር ላይ እንገኛለን፡፡
2. አንድነት ለግለሰብ፣ ለማህበረሰብና ለሀገር ብልጽግና ወሳኝ መሆኑን ዲናችን በእጅጉ ያስተምረናል፡፡
3. መውሊድና ጥቃቅን ልዩነቶች የጎንደርን ሙስሊም አይከፋፍሉትም፤አንድ ነን! የሚል ይዘት ያላቸው መነባንቦች የተበተኙ መሆኑንለማየት ችያለሁ፡፡
ከዚህ በመቀጠልም አህባሽ ለምን ተወገዘ? በሚል ርዕስ ሥር በተፃፈ ሌላው በራሪ ወረቀት
1. ሃሳባቸውን ያልተቀበሉ ሙስሊሞችንና ዑለማዎችን በማክፈሩ፣
2. በጣም ውስብስብና ሁሉም ሙስሊሞች በቀላሉ ሊረዷቸው የማይችሉ ነጥቦችን በማንሳት
ውዝግብ በመፍጠሩ፣
3.ሙስሊሙን ዑማ ወደ መጥፎ አቅጣጫ ሊመሩ የሚችሉ ጥራዝ ነጠቅ (ሻዝ) ፈትዋዎችን
መስጠታቸው፣
4.የአላህን ዲን ኢስላምን ለማጥፋት ከሚንቀሳቀሱ ይሁዳውያን ጋር ማበራቸው ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በአጠቃላይ የሙስሊሙን ዑማ አንድነት አደጋላይ ለመጣል የተቀመረ አስተሳሰብን ከጀርባው የደበቀ/ያዘለ አደገኛ የሙስሊም አንጃ በመሆኑ እኛ ሙስሊሞች እጅ ለጅ ተያይዘን አንድነታችን እንጠብቅ የሚሉና ተመሳሳይ በራሪ ወረቀቶች ተበትነዋል፡፡ ከሰላት በኋላ ያነጋገርኳቸው አዛውንት ዳዕዋውን እንዴት እንዳዩት ሲያስረዱ “ሞኛቸውን ይፈልጉ ድሮ ሳናውቅ ከወጣት ልጆቻችን ጋር ያናከሱን ይበቃል፤የኛ መመሪያ ቁርዓንና ሀዲስ ነው ስለዚህ ማንምሙስሊም በዚህ ከፋፋይ ስልጠና እንዲሳተፍ አንሻም ወደመጡበት ይመለሱ” በማለት ያለፈውን ስህተት አንደግምም ብለዋል፡፡ በጀመዓ ከመስጊድ ሲወጡ ያገኘኋቸው ወጣቶችም ስለ ዳዕዋው ምን ትላላችሁ የሚልጥያቄ አቅርቤላቸው ነበር፡፡ “ጎንደር ያፈራቻቸውን፣ በዓለም ላይ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አስተሳሰብ መቀየር ምክንያት የሆኑትን፣የኢትዮጵያ ምርጥ ዳዒዎቻችን በጎንደሩ የአህባሽ ፊታውራሪ ሙስጦፋ አሚኑ ካፊር መባላቸው፣ዛሬ ደግሞ በሊባኖሱ ዳዒ ፊታውራሪ የዓለም ታላላቅ ዓሊሞች ካፊሮች ናቸው መባላቸውን ስንሰማ “ነግ በኔ ብለናል” ነበር ያሉኝ፡፡ ስለዚህ “ሳይቃጠል በቅጠል” ነውና በሚቀጥለው ሳምንት በተክቢራ አህባሽ ከጎንደር ይባረራል” በማለት በምሬት ነበር የመለሱልኝ፡፡ ስልጠናውን በተመለከተም “ካላበደ በቀር ዱባ ቅል አይጥልም” ያላበደ፣ ረብጣ ብር የተቀበለ ወይም እንደነ ሙስጦፋ አሚኑ በነጋ በጠባ በአውሮፕላን ከጎንደር አዲስ አበባ የሚመላለስ ካልሆነ በስተቀር የሚሳተፍ ያለአይመስለንም በማለት በግርምት አጫውተውኛል፡፡ እኔም ከመስጊድ የወጡትን ሀሳብ ለመሰብሰብ ስባዝን ውየ ለምሳ ወደ ቤቴ አመራሁላቸሂሁ፡፡ በአጠቃላይ የህዝበ ሙስሊሙን ሀሳብ ስረዳ “አህባሽ የዘመኑ ረባሽ” በጎንደር ቦታ የላችሁም ሌላ ምሽግ ፈልጉ እያላቸው እንደሆነ ነው፡፡ አላሁ አክበር!!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 6, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: