RSS

ዜና ጎንደር አህባሽ በጎንደር ሰሞነኛ ወሬ “ከወደቁ ወዲያ መፈራገጥ መመላለጥ”

06 Apr

ዜና ጎንደር
አህባሽ በጎንደር ሰሞነኛ ወሬ
“ከወደቁ ወዲያ መፈራገጥ መመላለጥ”
ባለፈው ዘገባየ አህባሽ ከመጋቢት 19-24/2004 በጎንደር ከተማ ስልጠና አዘጋጅቶ እንደነበርና ስልጠናው ገና ከመጀመሩ “እናንተ እነማን ናችሁ” የሚል ፈተና ገጥሞት እንደነበርና ፍላጎት ሳይኖራቸው በግድ ስልጠና እንዲገቡ ከተደረጉት የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ስልጠና ካልመጣችሁ ከሥራ ትባረራላችሁ ተብለው ስልጠናው እየመረራቸው እንዲጨርሱ የተደረጉት ምስኪን ኡለማ ኢማሞች እንደነበሩ እንዲሁም ስልጠናው በአጠቃላይ የታለመለትን ግብ ሳይመታ በውርደት እንደተጠናቀቀ ዘግቤ ነበር፡፡የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብም “እኛ ድሮ የተሞኘነው ይበቃናል ከእንግዲህ ማንም እየመጣ ኺላፍ የሚያስነሱ ነገሮችን ብቻ እየመራረጡ ሙስሊሙን በሚበትኑ ሙስሊም መሳይ አጃዎች አንታለልም” በማለት አህባሽን እንዳይነሳ አድርገው ጥለውት ነበር፡፡
በከተማው የሚገኙ ታላላቅ ዑለማዎቻችንም “አሻፈረን እኛ ታላላቅ በዓለም የነበሩና ያሉ ኡለማዎችንም ሆነ የአህባሽን አስተሳሰብ አንቀበልም ያሉ ሙስሊሞችን አናከፍርም፣ ከሊባኖስ የመጡት “አይሁድ ቅብ” የአህባሽ ኡለሞች በእውቀት ከኛ ቢያንሱ እንጂ በጭርሽ አይበልጡም፣በሱፊያ ስም ሊነግዱ ሊያጭበረብሩ አይችሉም፣ኪታቦቻቸውን አይተናል አስተንትነናል ከኢስላም የሚያወጡ አያሌ ነገሮች አሉ፤ ስለዚህ እኛ ከስራ ተባረን በርሀብ እንሞታለን እንጅ በጭራሽ አይሆንም፣የአህባሽ ን አስተሳሰብ አንቀበልም” በማለት ሰሞኑን ትልቅ ዘመቻ ሲያደርጉና ሙስሊሙ የአንድነት መንፈስ እንዲኖረው ሲንቀሳቀሱ ሰነበቱ፡፡ውጤቱም ያማረና በተለይ ወጣቱ ጥሩ የአንድነት ስሜት ፣የመተሳሰብና “እኛ ሙስሊሞች እንጅ ሌላ ስያሜ የለንም” እስከማለት የደረሰ አንድነትን ሲያንጸባርቅ ሰነበተ፡፡ሁሉም ውስጡ ተደሰተ፡፡እኔም የዚሁ ደስታ ተካፋይ ነበርኩ፡፡
ታዲያ ይህ ደስታ፣የአንድነት ስሜት፣የሙስሊም ወጣቶች ፍቅር ያላስደሰተው በጎንደር የአህባሽ ፊታራሪ በሙስጦፋ አሚኑ የሚመራው አንጃ አዲስ እስትራቴጂ ይዞ ብቅ አለ፡፡አጅብ ነው፡፡ድሮ በታላቁ የጎንደር አሊም በነበሩት በሸህ መሀመድ ደሴ ስም በሚጠራውና ታላላቅ ዳዒዎችን ባፈራው ዛሬ ደግሞ በጎንደር የአህባሽ ምሽግና መነሀሪያ በሆነው በሸህ መሀመድ ደሴ (አላህ ይዘንላቸው)መስጊድ የተጠነሰሰው ይህ እስትራቴጂ ከመጋቢት 19-24/ 2004 በተሰጠውና ፍሬ ባላፈራው ስልጠና የተመሰረተና ሙስሊሙን እንደገና ሊበትን ይችላል ያሉትን ያቋም መግለጫ በየመስጊዱ በጀሌዎቻቸው አማካኝነት ማነብነብ ጀምረዋል፡፡ በዚህ የአቋም መግለጫ ስልጠናው ከመንግስት ጋር በመተባበር የተዘጋጀና በዘመኑ ቋንቋ “ውሀብያን፣አክራሪነትን፣አሸባሪነትን ፣ጥቂት የአክራሪነት ስሜት ያላቸውን ሰለፍዮች በኔ ግምት ሱፊ ቅብ የአህባሽ አስተሳሰብን የማይከተሉ በነርሱ አጠራር (ካፊሮችን) ለመደምሰስ የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብ ከጎናቸው እንዲቆምልመና አይሉት ጥያቄ ቢያቀርቡም ሙስሊሙ “ጀሮ ዳባ ልበስ” በማለት ላለማዳመጥ መስጊድ ውስጥ ጥሏቸው ወጥቷል፡፡የሚገርመው አንድ ነገር አለ፡፡እኔ የማውቀው የአቋም መግለጫ የሚቀርበው ስልጠናው ሲገባደድ መሆኑን ነው፡፡የጎንደር የአህባሽ አመራሮች ግን ገና ለአመራር ያልበቁ ደካማ መሆናቸውን የሚመላክት ተግባር ነው፡፡ስልጠናው ከተጠናቀቀ ከ42 ቀናት በኋላ የአቋም በግለጫ ማነብነቡ ለምን አስፈለገ? ለነገሩ በወቅቱ ለማን ያቀርቡታል! የተሳታፊው ቁጥር እጅግ አናሳ ነበር፡፡መግለጫውም አዲስ አበባ በሚገኙ የአህባሽ አመራሮች ካለተዘጋጀ እዚህ ማን ያዘጋጅላቸዋል፡፡ስለዚህ ተሰርቶ እስኪመጣ መጠበቅ ነበረባቸው ማለት ነው፡፡ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡
አጭር መልዕክት ለጎንደር የአህባሽ ፊታውራሪዎች፣ቀኛዝማቾችእ ንዲሁም ጀሌዎች
ጎንደር ድሮ እነ ሸህ ዓሊ ጎንደርን፣ሸህ መሀመድ ደሴን፣እነሸህ አብዱል ባሲጥን፣እነ ሀጅ ኤሊያስን(አላህ ዘንላቸው) እንዲሁም ሌሎች ታላላቅ ዓሊሞችን ያፈራች አሁንም እንደ እነኡስታዝ ሀሰን ታጁን፣ ኡስታዝ በድሩ ሁሴንን፣እነ ኡስታዝ ያሲን ኑሩን እንዲሁም ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው አያሌ ዳዒዎች ሀገር በመሆኗ የጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብን በቀላል ከኢስላም እናወጣዋለን ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው እላለሁ፡፡ምናልባት አህባሽ በሚሰጣቸው ደጎስ ያለ ገንዘብ በሚሰጣቸው ፊታውራሪዎች አይዟችሁ ባይነት በሚመራው አንጃ ጎንደር ላይ አህባሽ ድል አደርጋለሁ ብሎ አስቦ ከሆነ በታሪክ ትልቁን ስህተት ተሳሳተ ብየ መናገርእፈልጋለሁ፡፡ስለዚ ህ የጎንደር የአህባሽ ፊታውራሪዎች፣ቀኛዝማቾች እንዲሁም ጀሌዎች የጎንደር ሙስሊምህብረተሰብ ከዚህ ከፋፋይ ተግባራችሁ እንድትቆጠቡ በአላህ ስም ይጠይቃችኋል፡፡የእናንተ ተከታይ ያልሆነውን አታክፍሩ፣እናንተን ያልተከተሉ ዑለማዎቻችንን አታክፍሩ፣አትከፋፍሉን፣እ ኛ ሙስሊሞች ነን፡፡
ለጎንደር ሙስሊም ህብረተሰብ፤ የአህባሽን ሴራ በንቃት ልንከታተል ይገባል፡፡እኛ የአህባሽ ምሽግ ልንሆን አይገባም፡፡ለወደፊት ለሚደረገው የመጅሊስ አመራር ምርጫ፤ምርጫው መካሄድ ያለበት በመስጊድ እንጅ በቀበሌ መሆን እንደሌለበት፤መመረጥ ያለባቸው እንደድሮው በባላባትነት፣ በዘር እንዲሁም በሀብት ሳይሆን ሙስሊሙን በትክክል ያስተዳድሩታል፣ኡለማዎቻች ን በአላህ(ሱ.ወ) እና በረሱል(ሰ.ዐ.ወ.) መንገድ ሊመሩን የሚችሉ ዓሊሞችን የሚተኩልንንና እውቀት ያላቸውን ሙስሊም ወንድሞቻችንን በመስጊዶቻችን እንድንመርጥ በአላህ ስም እጠይቃለሁ፡፡ ለዛሬው በዚሁ ላብቃ፡፡አላህ በሰላም ያገናኘን፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 6, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: