RSS

በጎንደር ከተማ እየተሰጠ ያለዉ የአህባሽ ስልጠና አመርቂ ዉጤት እያሳየ አለመሆኑ ተገለፀ

06 Apr

በጎንደር ከተማ እየተሰጠ ያለዉ የአህባሽ ስልጠና አመርቂ ዉጤት እያሳየ አለመሆኑ ተገለፀ:: መጅሊስ በከፍተኛነት አሰፍስፎ ይጠብቅ የነበረዉ የጎንደር ሙስሊምን የማጥመቅ ዘመቻ የከተማዎ ሙስሊሞች ሴራቸዉን ቀድመዉ በመረዳታቸዉ በስልጠናዉ ላይ የተጠበቀዉን ያህል እየተሳተፍ አለመሆናቸዉን የአካባቢዉ ምንጮች ገልፀዎል:: ለስልጠና እንዲሳተፍ ከሁሉም መስጂዶች እና ጃሚአዎች ወደ 600ሰዎች ጥሪ የተደረገ ሲሆን በስልጠናዉ ላይ ግን 70ሰዎች ብቻ መካፈላቸዉን ምንጮች ገልፀዎል:: በስልጠናዉ ላይ ሲሳተፍ የነበሩት ሰዎችም ከቀን ወደ ቀን ቁጥራቸዉ እያሽቆለቆለ እንደሆነም ምንጮች ጨምረዉ ገልፀዎል:: በከተማዎ ሙስሊሞች ዘንድ የተበተነዉ የአቶ አህመድን አብዱላሂ ጨሎ እና የአይሁዳዊዉ ሀጋይ ኢንሪች ፎቶ የከተማዎን ሙስሊም ያስገረመና መነጋገሪያ መሆኑንም ተገልፆል:: በከተማዎ ላይ ከዚህ ፎቶ በተጨማሪ ሙስሊሙን ወደ አንድነት የሚጠሩ ፓፍሌቶች መበተናቸዉም ምንጮች ገልፀዎል:: ስልጠናዉ ከመጀመሩ በፊት የአህባሹ ፊት አዉራሪ ሙስጠፉ አሚኖ የተባለዉ ግለሰብ በጁምአ እለት ህዝቡ በተሰበሰበበት ታላላቅ የአለም የኢስላም ምሁራኖችን ካፊሮች ናቸዉ ማለቱ ህዝቡን ማሳዘኑና ማስቆጣቱ ተገልፆል:: አይሁድ ሰራሹ አህባሽ የኢትዮጲያን ሙስሊሞች አይለያይም!!! በከተማዎ ሙስሊሞች ዘንድ የተበተነዉ ሙስሊሙን ወደ አንድነት ከሚጠሩ ፓፍሌቶች መካከል: አብሽሩ! ቤታችን ሰፊ ነው::
ሰፋ ሰፋ በሉ!
ዲነል ኢስላም ሰፊ ቤት ነው:: “ላኢላሃ ኢለሏህ ሙሀመዱን ረሱሉሏህ” ብለው የመሰከሩ ሰዎችን ሁሉ ያስተናግዳል:: አርካነል ኢይማንና አርካነል ኢስላምን የተቀበለን ሁሉ በዕቅፉ ያኖራል:: ዲናችን ሰፊና የዑመት ዲን ነው! የተወሰኑ ግለሰቦችወይም ጀማዓዎች ብቻ ዲን አይደለም:: ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች ያመነን ሁሉ በስሩ ያካትታል:: ዝርዝር የሃሳብ ልዩነቶችን ለዓዋቂዎች ምርምር (ኢጅቲሃድ) ይተዋል:: እነኝ ዝርዝር የሃሳብ ልዩነቶችም አንድነትን የሚበታትኑ ነጥቦች አለመሆናቸውን ያስተመራል::
እኛ ሙስሊሞች :-
– ጌታችን አምሳያ የሌለው አንድ አሏህ(ሱ.ወ.): – ነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) አንድ:- ቁርዓናችን አንድ: – ቂብላችን አንድ…….
ስለሆነም ዲናችን አንድ ነው:: አሏህ(ሱ.ወ.)እንዲህ ዓይነት መሰረቱ የነጠረ ዲን ሰጥቶን: ሰፊና ዑመተል ኢስላምን ሊያስተናግድ የሚችል ያማረ ዲን ባለቤቶች ሆነን ለምን ይሆን አንዳንድ ግለሰቦች ዑማውን ለመከፋፈል መጣራቸው?! ለምን ይሆን ከፍቅር ይልቅ ጥላቻን: ከአንድነት ይልቅ መበታተንን: ከወንድማማችነት ይልቅ ጠላትነትን ለማስፈን ደፋ ቀና ማለታቸው?!
ለምን ይሆን ሙስሊሙን ዑማ አንድ ሊያደርጉየሚችሉ መሰረታዊ ነጥቦችን ችላ በማለት ዝርዝርና ሁሉም ሙስሊም እኩል ሊረዳቸው የማይችሉ ነጥቦችን እያነሱ ውዥንብር የሚፈጥሩ አስተምህሮቶችን ማፋፋማቸው?! ኢማን የማይጨምሩ ወይም ወደ መልካም ስራ የማይገፋፉ:_ ከመጨቃጨቅ: ቀልብን ከማድረቅና ለሙስሊሞች ጥላቻን ከማዳበር ያልዘለሉ ትምህርቶችን ስልጠና በሚል ስም ማስፋፋቱ ለምን ይሆን?
ሰፊው የኢስላም ቤት ውስጥ በፍቅር መኖር ይቻላል:: ወንድማማችነትን ጠብቆ በ“ላኢላሃ ኢለሏህ ሙሀመዱን ረሱሉሏህ” ገመድ መተሳሰር ይቻላል:: ረሱላችን (ሰ.ዐ.ወ) የጀነት መግቢያ ቁልፍ ያደረጉትስእኛው እርስ በርስ ያለንን ፍቅር አይደል?!
“لاتدخلوا الجنة حتى تؤمنوا, ولاتؤمنوا حتى تحابوا …..”
“ እስካላመናችሁ ጀነት አትገቡም:: እስካልተዋደዳችሁ ደግሞ ኢማናችሁ ሙሉ አይሆንም::…..” ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)::
ይህ እንዳይሆን አንድነትን ሊበትኑ: በዑማው ውስጥ ጥላቻን ሊያሰፍኑና በመጨረሻም ዲናችን አደጋ ላይ ሊጥሉ ሌት ተቀን የሚባዝኑ የዋሆችን “ ክፍፍል ይብቃን! ቤታችን ሰፊ ነው” ልንላቸው ይገባል::
“ በሰፊው እስልምና ውስጥ ጠባብ ጎጆ ቀልሳችሁ ይህ ነው እስልምና እያላችሁ ዑማውን አትበጥብጡ:: እስልምና ከናንተም ሆነ ከአስተሳሰባችሁ በላይ ሰፊ ነው::” ተብሎ ሊነገራቸው ይገባል::
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሙስሊሙ መካከል ልዩነትን በማስፋት የሚታወቁ: ታላላቅ የዓለማችን ዑለማዎችንና ዱዓቶችን “ካፊሮች” በማለት የሚዳፈሩና ከአይሁዶች ጋር ከፍተኛ ትስስር እንዳላቸው በመጥቀስ በ2005 እ.አ.አ. የአዝሃር ሙፍቲ ፕሮፌሰር ዓሊ ጁሙዐ ፈትዋ የሰጡባቸው “አህባሾች” በታላላቅ ዑለማዎቻችንና አባቶቻችን ከተሰሩ መስጅዶቻችን ገለል ሊሉይገባል::
ሊባኖስን በእርስ በርስ ግጭት እንጅ በዒልም አናውቃትም:: ሙስሊሙን የተለያየ ስያሜ በመስጠት እርስ በርስ የሚያጋጩና ሀገራችን ዐሊም ባላጣችበት ማንነታቸውን የማናቃቸው ጸጉረ-ልውጥ ሊባኖሳዊያን መስጅዶቻችን ውስጥ ጥላቻን የሚያሰፍኑ ትምህርቶቻቸውን ያቁሙልን:: እነኝህን ሰዎች አጅበው የመጡ ግለሰቦችም የጎንደርንሙስሊም ህብረተሰብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል::
እየተፈጸመ ያለውን ሙስሊሙን የመከፋፈል ተንኮል ለማክሸፍ የሚከተሉትን ሰላማዊ እርምጃዎች ብንወስድ መልካም ነው እንላለን::
1. በአህባሾች እየተሰጠ ካለው ስልጠና ራስንና ቤተሰብን ማግለል::
2. አንድነትን ሊፈረካክሱ ከሚችሉ አስተሳሰቦች ህብረተሰባችን እንዲርቅና በ“ላኢላሃ ኢለሏህ ሙሀመዱን ረሱሉሏህ” ገመድ እንዲተሳሰር ንቃት መፍጠር::
3. ከጭቅጭና ቀልብ ከሚያደርቁ ክርክሮች ይልቅ ሙስሊሙን በሚጠቅሙ የልማት ስራዎች በትጋት መሳተፍ (ለምሳሌ በከተማችን የየቲሞች ማሳደጊያ የበድር ፕሮጀክት ዕውንይሆን ዘንድ ንቁ ተሳታፊ መሆን)::
4. ሙስሊሙን ከሚያለያዩ አጀንዳዎች ይልቅ ሙስሊሙ አሏህን እንዲፈራ: ከዲን የራቁ ወጣት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ወደዲን እንዲመለሱ የሚያስችሉ ትምህርቶችን በየመስጂዱ ማስፋፋት::
5. ሁላችንም ወደ አሏህ በመመለስና ዐውፍ በመባባል በዲናችንም ሆነ በዱንያችን ላይ የሚመጣን በላእ ሁሉ አሏህ(ሱ.ወ.) እንዲመልስልን ዱዓ ማድረግ::
አሏህ ሆይ! አንድነታችን ከሚበታትኑ የአይሁድ ተልዕኮዎች ዑማውን በሙሉ እንድትጠብቅልን በሃያልነትህ እንለምንሃለን:: አንተ ሃያልና አሸናፊ የሆንክ ጌታ ነህና!
በታላቁ ነቢይ ሙሃመድ ላይ ሰላትና ሰላም ይውረድ!
አሏሁ አክበር ወሊላሂልሃምድ

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 6, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: