RSS

በዛሬዉ እለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች የሚኖሩ ሙስሊሞች ከመንግስት አካላት ጋር የመጅሊስን ምርጫ አስመልክተዉ ዉይይት አካሄ

06 Apr

በዛሬዉ እለት በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በሚገኙ ወረዳዎች የሚኖሩ ሙስሊሞች ከመንግስት አካላት ጋር የመጅሊስን ምርጫ አስመልክተዉ ዉይይት አካሄዱ:: በስብሰባዉ ላይ በየወረዳዉ ካሉ መስጂዶች ጥሪ የተደረገላቸዉ ሙስሊሞች የተሳተፍ ሲሆን በመንግስት በኩል የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ አቶ አብደላ እና የክ/ከተማዉ ስራ አስፈፃሚዎች ተገኝተዎል:: ከመድረክ በኩል የመጅሊስን ምርጫ አስመልክቶ የመንግስትን አቖም አቶ አብደላ ያብራሩ ሲሆን ከዚህም መካከል መንግስት ምርጫዉን አስመልክቶ 3 መሠረታዊ ፍላጎቶች አሉት ብለዎል:::: እነሱም 1) ምርጫዉ በሰላም እንዲካሄድ እና እንዲጠናቀቅ 2) ሁሉንም ሙስሊም ማህበረሰብ ያማከለ ምርጫ እንዲካሄድ እና 3) ፀረ ህገመንግስት የሆነ አስተሳሰብ ያላቸዉ ሰዎች ሾልከዉ በምርጫዉ እንዳይገቡ መንግስት ይፈልጋል ብለዎል:: መንግስት የሙስሊሙ ጥያቄ የመጅሊስ ምርጫ ከተካሄደ ሁሉም ጥያቄ ከዛ ቡሀላ ይፈታሉ ብሎ ማመኑን የገለፁ ሲሆን የምርጫዉ ባለቤት በቅድሚያ ህዝበ ሙስሊሙ ነዉ ቀጥሎም መጅሊስ ነዉ ከዛም በመቀጠል የመጅሊሱ መተዳደሪያ ደንብ ነዉ በማለት የምርጫዉን ሁኔታ ገልፀዎል:: ምርጫዉ የሚካሄደዉ በመጅሊስ የመተዳደሪያ ደንብ መሰረት ነዉ ያሉ ሲሆን ምርጫዉ በየወረዳዉ እንደሚካሄድ እና አስመራጩም ተመረጩም በአንድ ቀን ህዝቡ መርጦ አስመራጩ የሚመረጡትን ሰዎች ከህዝቡ ጥቆማ በመቀበል በድምፅ ብልጫ የተመረጠዉን ሰዉ እና የወደቀዉን እዛዉ አሳዉቀዉ በአንድ ቀን ምርጫዉ እንደሚጠናቀቅ ገልፀዎል:: በአዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች ምርጫዉ ሰኔ 30 እንደሚካሄድ በመግለፅ መንግስት ያለበትን ግዴታ እንደሚወጣና የቀረዉንም ነገር በዉዴታ እንደሚያግዝ ለተሰብሳቢዉ በመግለፅ መድረኩን ለተሰብሳቢዎች ክፍት አድርገዎል:: የክ/ከተማዉ ሙስሊሞችም የተለያዩ ጥያቄዎች ሰንዝረዎል::ከነዚህም መካከል መንግስት የሙስሊሙን ጥያቄ አልተረዳዉም ማለት ነዉ:: ሙስሊሙ የመጅሊስ አመራሮች ይዉረዱ ማለት ምርጫ ያካሂዱልን ማለት አይደለም:: ለምን ምርጫዉን መጅሊስ ያካሂደዎል? የምርጫዉ ቦታ በየመስጂዱ ነዉ መሆን ያለበት:: አለበለዚያ አሁንም የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይኖርበታል:: ምርጫዉ በመጅሊስ መተዳደሪያ መሠረት ነዉ የሚካሄደዉ ለተባለዉ መተዳደሪያ ደንቡ የተዘጋጀዉ በጣም የቆየ በመሆኑና የመጅሊስ አመራሮች እንዲመቻቸዉ ባስተካከሉት መተደደሪያ ደንብ እና ሁሉንም ሙስሊም የማያሳትፍ በመሆኑ አንቀበለዉም:: መንግስት ለምን ኮሚቴዎቻችንን አሸባሪ ፀረ-ህገመንግስት ናቸዉ እያለ ለምን ይሳደባል? መንግስት በምርጫዉ ዙሪያ ስላሰበዉ ነገር ለምን ከኮሚቴዎቻችን ጋር አይወያይም? የደረሰበትንም ዉሳኔ ለምን በኮሚቴዎቻችን በኩል ለህዝቡ እንዲደርሱ አይደረጉም? ለምን ኮሚቴዎቻችንን ማግለል አስፈለገ? ምርጫዉ በጣም ቀረበ? እንዴት ነዉ የመራጭነት ምዝገባን በተመለከተ እና በርካታ ጥያቄዎችን ተሰብሳቢዎቹ አንስተዎል:: ለተነሱት ጥያቄዎች አቶ አብደላ የሚከተለዉን ምላሽ ሰተዎል:: የመተዳደሪያ ደንቡን በተመለከተ መንግስት በሀይማኖት ጣልቃ ስለማይገባ መተዳደሪያ ደንቡን መቀየር አይችልም:: የመጅሊስ አመራሮች ምርጫዉን አያካሂዱ ካላችሁም የፈለጋችሁትን አስፈፃሚ መምረጥ ትችላላችሁ:: መንግስት በዚህ ጉዳይ ጣልቃ አይገባም:: ኮሚቴዎቹን በተመለከተ መንግስት ከመሬት ተነስቶ ማንንም አይወነጅልም:: ነገር ግን ከህገ መንግስቱ አንፃር የኮሚቴዉን እንቅስቃሴ ይከታተላል:: ህገ መንግስቱን እስካሁን ካልተፃረሩ ነፃ ናቸዉ ነገር ግን ከህገ መንግስቱ ዉጪ ከተንቀሳቀሱ ግን ከተጠያቂነት የማይድኑ መሆኑን ገልፀዎል:: የምርጫዉ ሁኔታ በኮሚቴዉ በኩል ለምን አይነገርም ህዝቡ በደስታ እንዲቀበላችሁ ተብለዉ ለተጠየቁት ሲመልሱ እዚህ አዳራሽ ዉስጥ የኮሚቴዉ አባል ካለ ይኸዉ ተነግሮታል ከሌሉም ደግሞ ባሉበት ወረዳ ሲነገር መስማት ይችላሉ በማለት ምላሻቸዉን ሰተዎል:: በዚህ ወቅት ተሰብሳቢዉ በከፍተኛ ሁኔታ የተቆጣ ሲሆን ኮሚቴዎቹን መሳደብ ማለት 99% ሙስሊሙን መሳደብ መሆኑን ልታዉቁ ይገባል:: ይህንን ጉዳይ ለበላይ አካል አቅርቡልን በማለት ቁጣቸዉን ገልፀዎል:: ምርጫዉ በጣም ቀረበ ለተባለዉ ጥያቄ ሲመልሱ እንዲሁም የአዲስአበባ ምርጫ ነዉ እንጂ የሚዘገየዉ ሁሉም ክልሎች ከሰኔ 30 በፊት ተካሂደዉ ያልቃሉ:: አሁንም ምርጫዉ እየተካሄደ ያለበት ቦታ አለ በማለት መልሰዎል:: ምርጫ በየመስጂዱ ይሁን ለተባለዉ መተዳደሪያ ደንቡ በየቀበሌዉ ስለሚል ህገ ደንቡን መንግስት መቀየር አይችልም ብለዎል:: ከንግግራቸዉ መግቢያ ላይ ምርጫዉ ፍፁም ፍትሀዊ እንደሚሆንና ኢህአዴግ ሂወቴ ከሚላቸዉ አራት ነጥቦች ዉስጥ አንዱ የሀይማኖት ነፃነት በመሆኑ ሙስሊሙ ሊሰጋ አይገባዉም ብለዎል::በመጨረሻም ስለመራጮች ምዝገባና ተያያዥ ጉዳዮች ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ያልሰጡ ሲሆን ተሳታፊዉ ጥያቄዎቻችንን አልጨረስንም በማለት እድል እንዲሰጣቸዉ ቢጠይቁም ሰብሳቢዉ አቶ አብደላ እያነሳቹ ያላቹት ጥያቄ መጅሊስን የሚመለከት እንጂ መንግስትን የሚመለከት ባለመሆኑ ስብሰባዉ በዚዉ ተቖችቷል በማለት ስብሰባዉ ተጠናቖል::

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 6, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: