RSS

በትላንትናዉ እለት ማክሰኞ 24/04/2012 በሱዳን ካርቱም በሚገኘዉ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ኢትዮጲያዉያን ሙስሊሞች በሱዳን የኢትዮጲያ አምባሳደር ጋር ዉይይት አካሄዱ

06 Apr

በትላንትናዉ እለት ማክሰኞ 24/04/2012 በሱዳን ካርቱም በሚገኘዉ አፍሪካ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ኢትዮጲያዉያን ሙስሊሞች በሱዳን የኢትዮጲያ አምባሳደር ጋር ዉይይት አካሄዱ:: በስብሰባዉም ላይ የዩኒቨርሲቲዉ ተማሪዎች ያላቸዉን ከፍተኛ ተቃዉሞ መግለፃቸዉን ምንጮች ጠቁመዎል:: በዉይይቱም መጨረሻ ላይ ተሰብሳቢዎቹ የአቖም መግለጫ በማዉጣት ስብሰባዉ መጠናቀቁን ምንጮች አስታዉቀዎል:: የአቖም መግለጫዉም እንደሚከተለዉ ይቀርባል: ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ-ካርቱም
እንደሚታወቀው መንግስታችን ከ1983 ዓ.ም ግንቦት 20 ጀምሮ ለኢትዮጵያ ያመጣው ለውጥ፦ በዴሞክራሲ ፣ በመልካም አስተዳደር ፣ በልማትና በኢኮኖሚ እንዲሁም በማህበራዊ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን- በተለይም ለሙስሊሙ ህ/ሰብ – ከፍተኛ እምርታ መሆኑን እኛ በአፍሪካ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲና በሌሎችም የሱዳን ዩኒቨርሲቲ እየተማርን ያለን የሙስሊም ተማሪዎች ይህን ጉዳይ በሚገባ እንረዳዋለን።
መንግስታችን በከፈታቸው ምቹ እድሎችና መስመሮች በመጠቀም እንደ ኢትዮጵያዊነታችን ከምንግስት ጎን በመቆም የሐገራችንን ህገ_መንግስትና ፖሊሲ በመከተል በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በሐገር መከላከልና በሌሎችም ዘርፈ ብዙ ሁልንተናዊ አስተዋጽኦ እያበረከትን መሆኑን ማንም ያማይክደው ነባራዊ ሐቅ ነው።
ለዚህም ነው በካርቱም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ኤምባሲ ከመቼዉም በላቀ መልኩ ከኛ ከሙስሊም ተማሪዎችጋር የኛን የልማት አስተዋጽኦ በመገዘብ በተለያዩ ጊዜያት ያገራችንን ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ዉይይት ማድረጉን አደንቀናል።
ነገር ግን መጅሊስና አሕባሽ በብዙሃኑ ሙስሊም ህብረተሰብ ላይ በፈጠሩት ሃይማኖታዊ ጫና ከህገ_ምንግስቱ አንቀጽ 27(በህገ- መንግስቱ ለይ የሰፈረውን አንቀፅ ፦1_ማንኛዉም ሰው የማሰብ፣ የህሊና እና የሃይማኖት ነጻነት አለው።ይህ መብት ማንኛዉም ሰው የመረጠዉን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል ፣ ሃይማኖቱንና እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግልጽ የማምለክ፣ የመከተል፣ የመተግበር፣ የማስተማር ወይም የመግለፅ መብትን ያካትታል። 2_ በአንቀጽ 90 ንዑስ አንቀጽ 2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ የሃይማኖት ተከታዮች ሃይምኖታቸዉን ለማስፋፋት እና ለማደራጀት የሚያስችላቸዉን የሃይማኖት ትምህርትና ያስተዳደር ተቋማት ማቋቋም ይቻላል። 3_ ማንኛዉም ሰው የሚፈልገዉን እምነት ለመያዝ ያለውን ነፃነት በሐይል ወይም በሌላ ሁኔታ በማስገደድ መገደብ ወይም መከላከል አይቻልም።4_……. …. 5_ እምነትን የመግለፅ መብት ሊገደብ የሚችለው የህዝብን ደህንነት፣ሰላምን፣ጤናን፣ ትምህርትን፣የህዝብን የሞራል ሁኔታ፣የሌሎች ዜጎችን መሠረታዊ መብቶች፣ ነፃነቶች፣እና መንግስት ከሐይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚመጡ ሕጎች ይሆናል።)
የሃይማኖት፣ የእምነትና የአመለካከት ነጻነት ከመፃረሩም በላይ በሐገሪቱ ላይ ከፍተኛ የሆነ አለመረጋጋት እየፈጠሩ ያሉመሆናቸውን እናምናለን።
ስለዚህ ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የአቋም መግለጫ በሚከተለው መልኩ አውጥተናል፦
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳይ አመራር ላይ ያሉት ግለሰቦች አይወክሉንም።
“አሕባሽ” የተባለው ቡድን በኢስላማዊ የሐይማኖት ተቋሞቻችን ላይ አስገድዶ ትምሕርት መስጠቱን እንዲያቆም።
በኢትዮጵያ ህገ-መንግስት “መንግስት በሐይማኖት ጣልቃ አይገባም” የሚለው አንቀፅ ይከበር።
ከላይ የተጠቀሱትን ሦስት መሰረታዊ የሙስሊሙን ጥያቄዎች በአወንታዊ መልኩ ታይተው መንግስታችን በጎ ምላሽ እንደሚሰጣቸው እምነታችን ሆኖ፤ ያለምንም ወንጀል የታሰሩ ሙስሊሞች እንድፈቱ፤ በችግሩ ምክንያት የተሰደዱ የመስጂድ መሪዎች ሰብአዊ መብታቸው ተጠብቆ ወደ መደበኛ ስራቸው እንዲመለሱ እንጠይቃለን።
“ልማት፣ዴሞክራሲ እና ሰላም፣ መልካም አስተዳደር፣ ለሰፊው ህዝባችን ይሁን!!!”
“ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ኮርታ ለዘላለም ትኑር!!!”
ግልባጭ፦
ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት
ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ፍትሕ ሚኒስቴር መ/ቤት
ለኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር መ/ቤት
በሱዳን የኢትዮጵያ ማህ/ሰብ ማህበር ጽ/ቤት

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 6, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: