RSS

ከትናንት ወድያ እሮብ may 16-2012 (ሜይ አስራ ስድስት ሁለት ሽህ አስራ ሁለት) በብራሰልስ በአውሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው እየደረሰ ነው ያሉትን የመብት ረገጣ በመቃወም ሰለፍ አድርገዋ

06 Apr

ከትናንት ወድያ እሮብ may 16-2012 (ሜይ አስራ ስድስት ሁለት ሽህ አስራ ሁለት) በብራሰልስ በአውሮፓ ኮሚሽን ፊት ለፊት ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው እየደረሰ ነው ያሉትን የመብት ረገጣ በመቃወም ሰለፍ አድርገዋል።በዚህ በተለይም በኢትዪጵያዊያን ሙስሊሞች እየተካሂደ ያለውን “የመብታችን ይከበር” እንቅስቃሴ በመደገፍና በሌላው የህብረተሰብ ክፍልም ላይ በአጠቃላይ ያለው የመብት ረገጣ ያቁም በማለት የአውሮፓው የበላይ ድርጅትም የራሱን ግፊት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ሰልፉን ያዘጋጁት በቤልጀም የሚገኙ ሶስት ድርጅቶች ማለትም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ድርጅት በቤልጀም፣ የአፋር የሰብአዊ ድርጅትና ሉቅማን የኢትዮጵያዊያን-ቤልጀማዊ ያን ሙስሊሞች ማህበር – ሲሆኑ ከሆላንድ፣ ከስዊድን፣ ከጀርመን፣ ከፈረንሳይና ከዩናይትድ ኪንግደም የመጡ ኢትዮጵያዊያን ተሳትፈውበታል። በሆላንድ የሰንሰለት የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ማህበርም ለሰልፉ ሙሉ ድጋፉን በመስጠት ተወካዮችን ልኳል።
ሰልፈኞች ያሰተጋቧቸው ከነበሩ መፈክሮች መካከል
– ገዳማትን ማጥፋት ታሪክን ማጥፋት ነው፤
– የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ጥያቄ ሰላማዊ እና የሰፊው ኢትዮጳያዊ የመብት ጥያቄ አካል ነው
– ኢስላማዊ መንግስት የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ጥያቄ አይደለም፤ ኾኖም አያውቅም፤
– ያለ ነጻነት እድገት የለም፤
– በአሳሳ አርሲ የተደረገውን የንጹሀን ዜጎች ጭፍጨፋ እናወግዛለን፤
– የአወልያ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ የቆመለትን አላማ እንደግፋለን፤
– አህባሽን በኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ለመጫን የሚደረገው ጥረት ይቁም፤
– ለሀይማኖታቸው ነጻነት የሚታገሉትን በሽብርተኝነት መፈረጁ ያቆም፤
– በእስር ላይ የሚገኙ የሀይማኖት አባቶች፣ የፓለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞች በአስቸኳይ ይፈቱ፤
– የሀስት ፕሮፓጋንዳ ለምብታችን መከበር የምናደርገውን ትግል አያዳክመውም፤
– በአፋር በጋምቤላ በቤኒሻንጉልና በሌሎችም ቦታዎች የሚካሄደው ዜጎችን የማፈናቀል ድርጉት ይቁም፤
የሚሉና አገራዊና ህዝባዊ ይዘት ያላቸው ነበሩ።
በዚህ በሜይ አስራ ስድስት የብራሰልሱ ትዕይንተ ህዝብ ላይ የሁለት ሺህ አምስት አገር አቀፉን ምርጫ ተንተርሰው ይደረጉ ከነበሩ ሰልፎች በኋላ ከተደረጉ ስለፎች ሁሉ በላጭነት ያለውም ነበር።
ከሰልፉ ቀደም ብሎ የሰልፉ አዘጋጅ ድርጅት ተወካዮች በኮሚሽኑ የውጭ አገልግሎት የኢትዮጵያ ደስክ ተጠሪ ከሆኑት ሚስተር ቶማስ ቮን ሖንደን ጋር ተገናኝተው በአገሪቱ ላይ አሉ ባሏቸውየመብት ጥሰቶች ላይ ተወያይተዋል። በተለይም አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄ ያለውን የሙስሊሙን እንቅስቃሴ በተመለከት መንግስት በተለያየ ወቅት የሰጣቸውን መገለጫዎች በመንተራስ ሁኔታው መንግስት ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆንየአፍሪካ ቀንድን እንዳለ ሊያቃውስ የሚችል አደገኛ ጨዋታ እያካሄደ በመሆኑ የአውሮፓ አገሮች ይህን ሁኔታ በመረዳት በመንግስት ላይ ጫና እንዲያደርጉ በሃላፊው በኩል አቤቱታቸውን አቅርበዋል።
በዚሁ ወቅት ቀደም በዲያስፖራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሲኖድ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያዊን ሙስሊሞች ላይ እየደረሰ ያለሁን ይመብት ጥሰት በመጥቀስ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ለመብታቸው መክበር በጋራ እንድነሱና እንዲታገሉ ያደረገችው ጥሪ በሙስሊሙም በክርስቲያኑም ሰፋ ያለ አድናቆትን እና ተቀባይነትን ተችሮታል።
የኢትዮጵያ መንግስት በሀይምኖት ዉስጥ ጥልቃ እየገባ ነው የሚለውን ክስ መሰረተ ቢስ በማለት በአገሪቱ እስልማዊ መንግስት ለማቋቋም የሚደረግ እንቅስቃሴ ስላለ እሱን ለማስቅም እየሰራሁ ነው በማለት መግለጫዎችን በተደጋጋሚ ሰጥቷል። ይህ በቤልጀም የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ይህን መንግስት የሚለውን የሚያመክን ሆኖ ተገኝቷል።
የሰልፉ አዘጋጅ ድርጅቶች በቀጣይ ተከታታይ የሆኑ በህዝቦች በመካክል መቀራረብን የሚፈጥሩና ትግላቸውንም ለማስተባበር የሚረዱ ፕሮግራሞች እንዳሏቸው ገልጸዋል።

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 6, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: