RSS

ዛሬ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል

05 Apr

ዛሬ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡ ምናልባትም የኛን ጉዳይ አስመልክቶ በጥልቀት እንደሚወያዩ ይገመታል፡፡ በመንግስት ሚዲያዎች እንደተገለፀው ኢህአዴግ 7000 ለሚሆኑ መካከለኛ ባለስልጣናት (ለፌዴራል፤ ለክልል፤ ለዞንና ለወረዳ ባለስልጣናት) ለ45 ቀን የሚቆይ ስልጠና ሊሰጥ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ስልጠናዎቹ በብር ሸለቆ፤ በጦላይና በአዳማ የሚሰጡ ሲሆን ወቅታዊ ጉዳዮችም ከስብሰባው አበይት አላማዎች እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ከዚህ በፊት ይደረግ እንደነበረው ‹‹የሃይማኖት አክራሪነትና የህዳሴያችን ጉዞ›› የሚል ሰነድ እንደሚቀርብ ይጠበቃል፡፡ ይህ ሰነድ የክርስትና አክራሪነትን ለይስሙላ ብቻ በማንሳት ‹‹እስላማዊ›› ያሉትን አክራሪነት በሰፊው ያትታትል፡፡ በሰነዱ መሰረት እስላማዊ አክራሪነት ምሳሌ ተደርጎ የተቀመጠው ቁርአን ተቀደደ እያሉ የሚያራግቡ፤ የቀደምት ነገስታት ጨቁነውናል እያሉ አቤቱታ የሚያቀርቡ፤ ሙሃደራ በሚባል የመንደር አደረጃጀት በመሰባሰብ የሚመካከሩ፤ ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የቅበላ እና የመሸኛ ፕሮግራም የሚያዘጋጁ፤ በትምህርት የደከሙትን በጥናት የሚደግፉ…..ሌሎች በርካታ ነጥቦች ተካተውበታል፡፡ ይታያችሁ እነዚህ በምን መስፈርት ነው አክራሪ (ወሃብያ) የሚያስብሉት፡፡ በተጨማሪም በሙስሊሙ እና በመስጂዶቹ ላይ ስለደረሱ ጉዳቶች (በጉራጌ ዞንና በሌሎችም) ምንም ሳይጠቀስ የጅማውን ጉዳይ የሚያብራራ ሌላ እራሱን የቻለ ሰነድ በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሲሆን በ45 ቀኑ ስልጠና ሰፊ ሽፋን እንደሚሰጠው ይጠበቃል፡፡ ይህንን ሰነድ ላነበበ ሰው ዋና አላማው ክርስቲያን ወገኖቻችንን በእኛ ላይ ለማነሳሳት ሆን ተብሎ የተዘጋጀ ነው የሚመስለው፡፡
ሁላችንም ከየአካባቢያችን ወደ ስልጠናው ሊገቡ ለሚችሉ አመራሮች አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲያገኙና በኢስላም ላይ ከሚያሴሩ ወገኖች ጋር ለተራ ጥቅም ሲባል እንዳይተባበሩ በተለያዩ ዘዴዎች ልንመክራቸው ይገባል፡፡ አቅራቢዎቹ ከተሳካላቸው አክራሪ ያሉትን ሙስሊም ጭራቅ አድርገው በመሳል ለማሳመን ካልተሳካላቸው ደግሞ ቅሬታ የሚያነሱትን በማሸማቀቅ በግድ ለመጫን እንደሚሞክሩ ከዚህ በፊት ካየናቸው የተለያዩ መድረኮች ታዝበናል፡፡ በመሆኑም ወደስልጠናው ሊገቡ ለሚችሉ ሙስሊምም ሆነ የሌላ እምነት ተከታዮች ጠንካራ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ከወዲሁ መሰራት አለበት፡፡ ለምሳሌ በየክልሉ የምንገን ሰዎች ጥያቄአችንን አስመልክቶ ኮሚቴዎቻችንን እስከአሁን ካስገቧቸው ደብዳቤዎች በመነሳት የራሳችሁን የግንዛቤ ማስጨበጫ ፅሁፍ በማዘጋጀት ማድረስ ለምትችሉት አመራር ሁሉ በአድራሻው ወይንም በአካል (ቢሮ እና በመኖሪያ ቤት) በማድረስ የተወሰነ ስራ ብንሰራ መልካም ነው፡፡ ይህ ስልጠና እንዳሰቡት የሚሳካላቸው ከሆነ ሙስሊሙን በተለይ በክልል እና በወረዳ ደረጃ እስከመጨረሻው ለማሸማቀቅ መንገዱን ይጠርጉበታል፡፡
በሌላ በኩል የውጭ ሚዲያ ድምፃችንን ማሰማት ተከትሎ ከፍተኛ የሆነ ውጥረት እንደተፈጠረ ምንጮች ዘግበዋል፡፡ የዜናው መዘገብ በኢንቨስትመንት፤ በቱሪዝም እና በሌሎች መሰል ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ስለሚኖረው መንግስት ለማስተባበል የሚጠቀመው እስትራቴጂ እኛን ሊጎዳ ስለሚችል በሁሉም መልኩ ከመቼውም ግዜ በላይ ልንጠነክር ይገባል፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 5, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: