RSS

ውድ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን

05 Apr

ውድ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን
አሁን ያለንበት ወቅት እጅግ ወሳኝ ከመሆኑም በላይ የኛ እና የቀጣይ ሙስሊሙ ትውልድ ህልውና የሚወሰንበትም ነው፡፡ በተለያዩ መድረኮች እንደሰማነውና እንዳነበብነው በኢትዮጵ ሙስሊሞች ላይ ሌላ ታሪክ ሊፈጥሩ እየሴሩ ነው፡፡
1. አቶ በረከት ስምኦን ከዚህ በፊት እንደተናገሩት ‹‹ወሃብያን ለማጥፋት ከዚህ በፊት ሞክረን ያለበቂ ዝግጅት ስለነበር የገባነው ለመመለስ ተገደናል፡፡ አሁን ግን ከባለፈው ድክመታችን ተምረን በጭራሽ ወደኋላ ላንል አስፈላጊውን ዝግጅት ሁሉ አድርገን ነው የገባነው›› በማለት የጀመሩትን ፀረ ኢስላም ዘመቻ እንደማያቆሙ በስብሰባ መሃል መዛታቸውን ምንጮች ዘግበዋል፡፡
2. ለከፍተኛ ባለስልጣናት አቶ አባይ ፀሃይ እንደተናገሩት ‹‹ስንት የደከምንበትን እና ሁሉም ባለስልጣናት ተሰባስበን እንደመንግስት ወስነን የገባንበትን ፕሮጀክት (አህባሽን የማስፋፋት) ሳናስበው እያኮላሹብን ነው፡፡ እንደመንግስት የወሰንነው ጉዳይ በመሆኑ በጭራሽ ወደኋላ አንመለስም፡፡
3. ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለባለስልጣናቱ በፕላዝማ እስክሪን እንዳስተላለፉት ‹አዚህ ያላችሁ ባለሰልጣናት ጨምሮ ወይ ከውሃብያ ወይ ደግሞ ከኢህአዴግ መምረጥ ይኖርባችኋል፡፡ ሁለቱንም መሆን አይቻልም›› ማለታቸውን ምንጮች ዘግበዋል፡፡
4. ዶክተር ሽፈራው የሚባሉት የዘባረቁትን ማንሳት አያስፈልግም
የተወደዳችሁ ሙስሊሞች
ቢያንስ በዚህ ሰዓት የበደላችን ምንጭ መንግስትና መንግስት ብቻ እንደሆነ የተሸወደም ከነበረ፤አውቆም ታግሶ የነበረ ካለ ግልፅ ሆኖለታል፡፡ ሙስሊሙን ከተሳካላቸው በአህባሽ ማጥመቅ ካልተሳካለቸው ደግሞ በተለያዩ ስያሜዎች በመከፋፈል እስከ ህዝብ ቆጠራ ድረስ የሚዘልቅ ሴራ እያጠነጠኑ ነው፡፡ ሱፊ፤ ሰለፊ ምናምን የሚሉት ለዛ ማዘጋጀታቸው መሆኑን አውቀን ዲናችንን እንጠብቅ፡፡
ግብፅን ለማስፈራራት እንዲጠቅማቸው አሜሪካንና እስራኤል ባጠመዱት ወጥመድ የራሳቸው የግል ጥላቻ ተጨምሮበት ሙስሊሙን አሳልፈው በመሸጥ ባንዳነታቸውን ሊያሳዩን ነው፡፡ስለ ኢኮኖሚ፤ ፖለቲካ እንዲሁም ማህበራዊ ነክ ጉዳዮች የማያስብ በቀደዱለት የሚፈስ ነፈዝ ትውልድ ሊፈጥሩ እየታተሩ ነው፡፡
እስኪ አስቡት የዛሬ 38 አመት በ1966 ነበር አባቶቻችን ባደረጉት የመብት ጥቄ ዛሬ እኔና እናንተ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሙስሊሞች ሳይሆን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተባልነው፡፡ የዒድ ቀናት ብሄራዊ በዓላት ሁነው ስራና ትምህርት እንዲዘጋ የተደረገው፡፡ ዛሬ ትውልዱ ወደኋላ የሄደ ይመስላል፡፡ ነገ የሚመጡት ትውልዶች በኛ ግዜ ያስቀመጥንላቸውን ‹አህባሽ ወይንም ሱፊ፤ ገነመሌ› የሚባል ስም መውረሳቸው ነው፡፡ ወገን ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ለታሪካዊው እረጅም ጉዞ እንነሳ፡፡
ልብ እንበል መንገዱ እረጅም ስለሆነ በአጭር የሚያስቀር ሩጫ አያዋጣም፡፡ በመሆኑም እንደከዚህ ቀደሙ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መንግስትን በቀጥታ ከእምነታችን ላይ እጅህን አንሳ ልንለው ይገባል፡፡ በሶስት ወራት የበደለንን መለየት ከቻልን በጥቂት ግዜያት ውስጥ ደግሞ እናሸንፋለን፡፡ አትጠራጠሩ ኢንሻአላህ፡፡
ሰዎቹ ጦርነት የገጠሙት ከሃያሉ አላህ (ሱ.ወ) ጋር በመሆኑ መንኮታኮታቸው የማይቀር ነው፡፡ ምናልባት ወደኢስላም የተቀሰሩ ጣቶች ሁሉ ዳግም ጣት መሆን ላይችሉ እንደሚቆረጡ የሚማሩበት ታሪካዊ አጋጣሚም እየመጣ ይሆናል፡፡ ግን በኛ በኩል ዛቻና ፉከራ ብቻ ሳይሆን የተግባር ሰዎች ልንሆን ይገባል፡፡ በዒባዳ መጠንከር፤ ዱዓ ማብዛት እና ከወንጀል መጠበቅን አደራ፡፡ እንደኔ እንደኔ በመስጂድ ውስጥ የአዳር ፕሮግራም ቢጀመር እላለሁ፡፡ እናንተስ፡፡

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 5, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: