RSS

ዛሬስ… ታዲያ ጠ/ሚኒስቴሩ ምን ነካቸው?

03 Apr

ዛሬስ… ታዲያ ጠ/ሚኒስቴሩ ምን ነካቸው?
በድር ኢትዮጲያ- ሚያዚያ 12/ 1966 የተካሄደውን የኢትዮጲያ ሙስሊሞች የመብት ጥያቄና ትዕይንተ ህዝብ አስመልክቶ በህይወት ካሉ የእንቅስቃሴው መሪዎች- ከነ ዶ/ር አህመድ ቀሎ ፤ አባ ቢያ አባ ጆቢር እና አቶ ሙሀመድ ሀሰን- ጋር በአንድ ወቅት ቃለ-መጠይቅ አድርጎ ነበር፤ ከዚያ ውስጥ በትንሹ ቀንጭቤ እናካፍላችሁ፡-
……..
በድር…… ያ ታሪካዊ ሰልፍ በሀገሪትዋ ታሪክ ከዚያን ቀደም የታየ እነዳልነበረ ተዘግቦዋል፤ የህዝቡ ብዛት እጅግ ብዙ እንደነበር ነው፡፡ ታዲያ ያ ታላቅ ሰልፍና መነሳሳት ያስገኘው ለውጥ ምንድነው ይላሉ? ከሰልፉ በፊት የነበረውን የሙስሊሙን ስዕል ምን ያህል ቀይሮታል?
አባ ቢያ….. መቼም በሁለት መንገድ ነው ውጤት የተገኘው፤ አንደኛው ወጣት አዛውንት መሻይሁ ሁላ ለካ መብት አለኝ? ለካስ ይህ ይገባናል? የሚል የህልውና ንቃት እንዲኖር አስችሏል፡፡ አወቀ ነቃ ማለት ነው፡፡ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ማንንም ሳይጎዳ ከሌሎች ጋር አብሮ ሆኖ (የዪኒቨርሲቲው ክርስቲያን ተማሪዎች አብረውን እንደወጡት ማለት ነው) መብቱን ማስከበር እንደሚቻል መብቱን ለመጠየቅ መብት እንዳለው ተረዳ፡፡ ሌላው ደግሞ ከእንዳልካቸው ካኒኔ በኋላ ወደ ስልጣን የመጣው ደርግ ይህንን ነገር አውቆት ነው የመጣው ስለዚህ ገና ከጅምሩ ከአላማው ውስጥ የነበረው “የሃይማኖት እኩልነት” የሚል ነበር፡፡ ኢስላማዊ በዓላት እውቅናን አገኙ፤ በጉባዔው ላይ ከርዕሰ-በሄሮች ጋር የሚቀመጡት ጳጳሶች ብቻ ነበሩ የሙሰሊሙ ተጠሪዎችም እንዲታከሉ ተደረገ፤ ጳጳሶቹ በማርቸዲስ ሲሄዱ ሀጂ ሙሃመድ ሳኒ (አላህ ይርሃማቸው) በእግራቸው ነበር የሚሄዱት እናም ለሳችውም በስተመጨረሻ መኪና ተመደበላቸው፡፡ ስለዚህ የሙስሊሙ ህልውና በመንግስት ደረጃም ሆነ በማህበራዊ ኑሮው አንፃር ከፍ አለ፡፡ ሰውም ይህንን ሲረዳ መስጂዶች እንዲሰሩ መጠየቅ ጀመረ፤ የሙስሊሙ ተወካዮች ከውጪው ዓለም ጋር ለመተዋወቅ ልዑኮቹን ወደ ውጭ ሃገራት መላክ መጣ ማለት ነው፡፡እዚህ ጋ መጥቀስ የምፈልገው መታለፍ የሌለበት ነገር የዛኔው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አብረውን የነበሩበት ጉዳይ ነው፡፡ ያኔ የነበረው የተማሪውን እንቅስቃሴ እነ ጌታቸው በጋሻው ሲመሩት ነበር፡፡ ሌሎች ደግሞ እነ መለሰ ተክሌ፤ ያሁኑ ጠቅላይ ሚኒስቴር የዛኔው ለገሰ ዜናዊ ስባሰባ ላይ አብረውን ይመጡ ነበር፡፡ እነ ዮሃንስ በንቲ፤ ኋላ ገላሳ ዲልቦ የOLF ሃላፊ የነበረው፤ እነ ሮቤርቶ ጀዛኖ እነ መራራ ጉዲና አሁን የኦብኮ ሃላፊ፤ አቡሃ ምትኩ፤ እሸቱ ጮሌ በርግጥ ያኔ እሱ አስተማሪ ነበር፤ እነ ፍቅሬ መርዕድ(ፕሮፌሰር)(በመን ግስቱ ኃይለማርያም ኩደታ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የጄኔራል መርዕድ መንገሻ ልጅ)፤ እነ ዮናስ አድማሱ እነዲሁም ሌሎች ታዋቂ ምሁራን በሚያስደስት ሁናቴ ነበር ከጎናችን የቆሙት፡፡ እንደው ትዝ የሚለኝና የማይረሳኝ የአሁኑ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሙስሊሞቹ ለሰልፍ ይዘውት የወጡትን መፈክሮች ከሚያፈልቁትና መፈክሩን ሲፅፉ ካደሩት ውስጥ አንዱ ነበሩ፡፡
…..
ዛሬስ…… ታዲያ ምን ሁኑ!? ምን ነካዎት!? ኧረ ይንገሩን!!! …. ኧረ ያናግሩን!!!!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 3, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: