RSS

በየመስጂዱ የሚካሄዱ የመብት ጥያቄዎችን አስመልክቶ የተሰጠ ግላዊ አስተያየት በየመስጂዱ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አላማቸው ሊሆን የሚገባው

03 Apr

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው
በየመስጂዱ የሚካሄዱ የመብት ጥያቄዎችን አስመልክቶ የተሰጠ ግላዊ አስተያየት በየመስጂዱ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች አላማቸው ሊሆን የሚገባው
• አወሊያ የተፈጠረው ሙቀት እንዳይቀዘቅዝ
• አወሊያ የማይመጡ የነበሩና በየመስጂዱ የሚገኙ ሰጋጆችን ይፋ የትግሉ አጋር እንዲሆኑ መቀስቀስ (ማግባባት)
• በቀጣ ይካሄዳል ተብሎ ስለሚጠበቀው ምርጫ አስፈላጊ ግንዛቤ ለመፍጠርና ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ
1. ከአላማዎቹ አንፃር መታሰብ ያለባቸው ነጥቦች
1.1. መንቀሳቀስ እንችልባቸዋለን ተብሎ በሚታሰብባቸው መስጂዶች በሙሉ በአንዴ አለመጀመር፡፡ ምክንያቱም፡-
• የሙከራ ትግበራ ከመሆኑ አንፃር ከመስጂድ ኮሚቴዎችም ሆነ ከሰጋጆቹ የሚቃወሙ ሊኖሩ መቻላቸውና ለዚያ የሚሆን መፍትሄ ባለመዘጋጀታችን
• ሁሉም ጋር በአንዴ ተጀምሮ በአንዴ በማጋለጥ መቆም ስለሌለበት
• ትግሉ ሲፋፋም ልንጠቀማቸው የሚገቡ መስጂዶች (አንዋር፤ ኑር፤….) ባልተደራጀ መልኩ ተጀምሮ ከባድ ስህተት እንዳይሰራ
1.2. እንቅስቃሴውን ለማካሄድ ጠንካራ ቅድመ ሁኔታዎች መቀመጥ አለባቸው፡፡ ለምሳሌ፡-
• መድረክ ያለምንም ፀብ ልንቆጣጠር በምንችልባቸው መስጂዶች ብቻ መጀመር የያ ከካለልሀሆነ ደገግመሞ ወጥነት ያለው ተቃውሞ ለማሰማት መጣር
• በየመስጂዱ መድረኩን የሚይዙት ሰዎች የዛ መስጂድ ቋሚ አባል መሆን ይኖርባቸዋል
• ተቃውሞው የሚካሄደው ለምንና እንዴት እንደሆነ ለህዝቡ የሚያብራራ (ሰው እና በራሪ ወረቀቶች) ማዘጋጀት
• ብቃታችንንም ሆነ የተገኙ ፋይዳዎችን ለመገምገም እንዲያመች የተለያዩ አካባቢዎችን ሊወክሉ በሚችሉ ወሳኝና ጥቂት መስጂዶች ብቻ ለዚህኛው ሳምንት መምረጥ
1.3. ቅድመ ሁኔታዎቹ ከተሟሉ ፕሮግራሙ ላይ የተሰጡ ጥቆማዎች
• የተቃውሞ ድምፃችን መልስ እንጂ ለሚመለከተው አካል የመድረስ ችግር ስለሌለበት የፕሮግራሞቹ ይዘት ከመጦዝ ይልቅ ግንዛቤ ማስጨበጥ ላይ ቢያተኩር፡፡ ለምሳሌ፡-
• አወሊያ ሳይመጣ የኖረውን ህዝብ ተመሳሳይ ወደ ሆነ የግንዛቤ ደረጃ ላይ ማድረስ
• በሂደቶቹ ላይ በሃገር ውስጥ (ክልሎችን ጨምሮ) እና ከሃገር ውጭ ያሉ ተመሳሳይ የመብት ጥያቄ ሂደቶችን ለህዝቡ መግለፅ
• መስጂዶቹ ከራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር የትግሉ ደጋፊ እንዲሆኑ ማሳመን
• በጥያቄዎቻችን ዙሪያ በሚዲያና በስብሰባዎች እየተነዙ ያሉ ብዥታዎችና ማብጠልጠሎችን ማጥራት
• መስጂድን ማእከል ለሚያደርጉ የምርጫ እንቅስቃሴዎች አስፈላጊውን ቅስቀሳ ማድረግ
• ከመስጂዱ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር መጅሊስንና አህባሽን ሊቃወሙ የሚችልባቸውን ነጥቦችን አንጥሮ በማውታት ለህዝቡ ማሳየት
• የምናቀርብለት ህብረተሰብ በተጨባጭ በልዩነቶች ውስጥ የሚኖር በመሆኑ ሁሉም በአንድነት ሊቃወማቸው በሚገቡ ነጥቦች ዙሪያ ብቻ ማተኮር (በይዘትም ሆነ በአካሄድ)
• የድምፅ ማጉያው ማሰማት እስከሚችልበት ድረስ የሚገኙ የሌላ እምነት ተከታዮችን ስለጥያቄአችን ምንትና አቅጣጫ ለማሳት ስለሚደረጉ አጉል አካሄዶች መልእክት በተዘዋዋሪ መንገድ ማስተላለፍ፡፡
2. የሚጠበቅ ውጤት
• ስለመጅሊስም ሆነ ስለአህባሽ ተቃውሞ በይፋ የሚገለፅባቸው መድረኮችን አስተማማኝ በሆነ መልኩ ማረጋገጥ
• የየመስጂዱ ጀመዓዎች በጥያቄዎቹ ዙሪያ ግልፅ እና ወጥ የሆነ አረዳድ ይኖራቸዋል
• በጥያቄዎቻችን ዙሪያ የሚረጩ ብዥታዎችን ሀሰትነታቸውን በበቂ ሁኔታ ማሳወቅ መቻል
• መስጂዶቻቸውን በንቃት በመጠበቅ ለቀጣይ ስራ በአንድነት የሚሰሩ ጀመአዎች መፈጠር
• በቀጣይ አወሊያ ለሚኖረው ፕሮግራም ለመሄድ በርካታ ጀመዓ ማነሳሳት
• ብዙሃኑ ሙስሊም ለሚስማማባቸው አካሄዶችና አስፈፃሚዎች ህዝቡ እውቅናና ድጋፍ አንዲሰጥ ይደረጋል
3. መፈፀም የሌለባቸው ስህተቶች
• እስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ያላቸውና በቀጣይ ዋና የትግል ማእከል መሆን በሚችሉ መስጂዶች ያለ በቂ ዝግጅት ተቃውሞ መጀመር የለበትም
• ሰዎችን በሞባይል መልእክት መጥራት አስፈላጊ አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ለመንግስት አካላት ቀድመው ለመከልከል እንዲዘጋጁ ያደርጋል
በተጨማሪም ጠላቶቻችን ብዙ ተዘጋጅተዋል ተቃውሞዋችንን በየ መስጊዱ እናደረጋለን ብለን ስናቅድ እነሱም በየ መስጊዱ ለመበጥበጥ አያስቡም አይባልም ! 90% ከመቶ የመረበሽ እድሉ አላቸው ምክንያቱም የተከለለ ግቢ የለውም ለፍተሻ አይመችም ወዘተ ስለዚህ ከ3 ወር በላይ በሰላማዊ መንገድ ሲጉዋዝ የነበረውን ትግል በ አቁዋራጭ ለማኮላሸት ብዙ ነገር ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ሁላችንም ፀጥታውን የማሰከበር ሃላፊነታችንን መወጣት ይኖርብናል ቀኑ ከመድረሱና ከመወዛገባችን በፊት መስመራችንን ብናዘጋጅና ግልፅ የሆነ አካሄድ ለሁሉም መስጂዶች ቢደርሳቸው፡፡ አላሁ አእለም!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 3, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: