RSS

በትላንትናዉ እለት እሁድ በጅማ ከተማ ጊቤ አዳራሽ መንግስት ከከተማዎ ነዎሪዎችጋር ዉይይት አካሄደ::

03 Apr

በትላንትናዉ እለት እሁድ በጅማ ከተማ ጊቤ አዳራሽ መንግስት ከከተማዎ ነዎሪዎችጋር ዉይይት አካሄደ:: ዉይይት መካሄድ የጀመረዉ ባሳለፍነዉ ማክሰኞ የጅማ ከተማባለስልጣናት በመሰብሰብ ሲሆን ከፌደራል መንግስት የመጡ ባለስጣናት ወቅታዊ የሆነዉን ጉዳይ አወያይተዎቸዎል:: በስብሰባቸዉም ላይ ወሀቢያ ፀረ ህገመንግስትና ፀረ ሠላም ሀይል መሆኑን በመንግስት መፈረጁን እና ሁሉም አካል በመረባረብ ይህንን ፀረ ህገመንግስት የሆነ ቡድንን መዎጋት እንዳለባቸዉ ገለፃአርገዎል:: በስብሰባዉ ላይ የተገኙ የከተማዎ ባለስልጣኖች በአንድነት በመሆን የተቃወሙ ሲሆን በከተማዎ ከፍተኛየልማታችን አጋር የሆኑት እገዛ ሲያስፈልገን በፍጥነት የሚደርሱልን አሁን ወሀብያ የምትሏቸዉ ሰዎች ናቸዉ ስለዚህ እንዲ አይነቱ ፍርድ ተገቢ አይደለም በማለት በአንድነት ተቃዉሞአቸዉን እንዳሰሙ ተገልፆል::ነገር ግን ተቃዉሞአቸዉ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቶ ከከተማዉ ባለስልጣናት ጋር የሚደረገዉ ዉይይት ለሁለት ተጨማሪ ቀናትእንዲቀጥል ተደርጎ ሀሙስ እለት ተጠናቆል:: በስብሰባዉ መጨረሻ ላይም ባለስልጣናቱ የከተማዎን የቀበሌ አመራሮች እና አስተዳዳሪዎች እንዲሰበስቡና ፀረ ህገመንግስት ነዉ የተባለዉን ወሀቢያ እንዲዎጉ እንዲያሳስቡ የቤት ስራ ተሰቷቸዉ ተጠናቆል:: በሚቀጥለዉ ቀንም ጁምአ የቀበሌ አመራሮች እና የከተማዉ አስተዳደር ክፍሎችን በመሰብሰብ የመንግስትን አቖም እንዲያዉቁ ተደርጎል::የከተማዎንም ነዎሪዎች እንዲሰበስቡና ስለ ፀረ ሰላም እና ፀረ ህገ መንግስት ስለሚባለዉ ወሀቢያ ህዝቡ ግንዛቤ እንዲያገኝ እንዲያረጉ ትዛዝ ተሰቷቸዉ ስብሰባዉ ተጠናቖል:: በትእዛዙም መሰረት ከከተማዎ ነዎሪዎች ዉስጥ በመምረጥ ታዎቂሰዎችን የከተማዎ ሽማግሌዎችን እና ትላልቅ ሰዎችን ጨምሮ ጥሪ በማድረግበትላንትናዉ እለት እሁድ ስብሰባዉን አካሂደዎል:: በሚያስገርም ሁኔታ ጥሪ የተደረገላቸዉ ሰዎች ተመርጠዉ ቢሆንም የከተማዉ ነዎሪዎች እርስ በርስ በመነጋገር ወደስብሰባ አዳራሹ በጠዎቱ መትመሙን ተያይዘዉት እንደነበር ተገልፆል:: የአዳራሹ ወንበር ለስብሰባ የመጣዉ ህዝብ በመብዛቱ ማስተናገድ አልቻለም ነበር:: ለዚህም ብለዉ በመኪና ከተለያዩ ቦታዎች ወንበር በማምጣት ህዝቡእንዲስተናገድ ጥረት ቢያረጉም የህዝቡ ቁጥር በመብዛቱ ተሳታፊዉ ቆመዉም ስብሰባዉን እንዲካፈሉ አስገድዷ ነበር:: የህዝቡ መብዛት ያስደነገጣቸዉ የመንግስት አካላት ሊያወያዩበት ያሰቡትን አጀንዳ በማስተካከል የከተማችንን ሰላም እንዴት እንጠብቅ በሚል እርእስ ለማወያየት ሞክረዎል:: ስብሰባዉ ይጀመራል የተባለዉ ከጠዎቱ 2:30 ቢሆንም የተጀመረዉ ግን 4 ሰአት ላይ ነበር::በዉይይቱም ላይ ቀስ በቀስ ስለወሀቢያም ለመነካካት የሞከሩ ሲሆን በሙስሊሞች በኩል የፒትሽን ማስፈረም እንቅስቃሴዉን ተቃዉመዎል::ምክንያቱን ሲገልፁ በከተማችን አህባሽ የሚባል ነገርሳይመጣና ሳይኖር የአህባሽን በመቃወም ፊርማ ማሰባሰቡ ተገቢ አይደለም በማለት ምክንያታቸዉን አስቀምጠዎል:: ከተሳታፊዎች በኩል አራት ሰዎች ብቻ አስተያየት የሰጡ ሲሆን የመጀመሪያዉ አስተያየት ሰጪ ከመድረክ በኩል የቀረበዉን ሀሳብ በሚያስደንቅ ሁኔታ ምላሽ በመስጠቱ በአዳራሹ የተገኘዉ ሙስሊሙም ሆነ ሌላ እምነት ተከተይ ድጋፉቸዉን በተክቢራና በጭብጨባ በመግለፅ አዳራሹን አናግተዉታል:: በሁለተኛነት አስተያየታቸዉን የሰጡት አንድ ሽማግሌ የሆኑ ቄስ ሲሆኑ በአስተያየታቸዉም እኔ በእድሜዬ የማዉቀዉ ሙስሊም ሲባል እና ወሀቢይ ሲባል እንናተ እንደምትሉት አይነቱን ሳይሆን በሌላ መልኩ የማዉቅ ሲሆን አህባሽ የሚባለዉን ግን በሂወቴ ሰምቼ አላዉቅም በማለት መንግስት እና ህዝቡ አዲስ ሀይማኖት የሆነዉን ወደ መጣበት እንዲመለስ እንዲያረጉ ጥሪ አስተላልፈዎል:: የተቀሩት ሁለት ተሳታፊያንም ተመሳሳይ ሀሳብ በመስጠት ተቃዉሞአቸዉን ገልፀዎል:: በስብሰባዉ መጨረሻ ላይም የዚህ አይነት ዉይይት በየቀበሌዉ በተዎረድ እንደሚኖር ከመንግስት በኩል ተገልፆ ስብሰባዉ ያለ ፍሬ ተጠኖቖል::ይህ ስብሰባ የሚያሳየን ሙስሊሙን በመከፉፈልና ከሌላ እምነት ተከታዮች ጋርም ለማቃቃር መታሰቡን ነዉ::የሙስሊሙ የመብት ጥያቄን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለማዞር እየተሞከረ መሆኑን ያሳየናል::አላህ ሴራቸዉን ያክሽፍባቸዉ!!!

Advertisements
 
Leave a comment

Posted by on April 3, 2013 in Uncategorized

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: