RSS

አወሊያ 8ኛውን ሳምንት የህዝብ ተቃውሞ አስተናግ ዳዋለች!

25 Feb

የሙስሊሙ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጥባቸው ለየካቲት 26 ቀጠሮ በተያዘበት ሁኔታ አወሊያ በዛሬው ዕለት ባልተጠበቀ የህዝብ ማዕበል ተጥለቀለቀች፡፡ በዕለተ ረቡዕ ምሽት ራዲዮ ፋና ያስተላለፈው ሚዛናዊነት የጎደለው ፕሮግራም የብዙሃንን ቀልብ ሰብሮ ከተቃውሞ የትዕይንት መድረኩ ያርቃቸዋል የሚል ግምት የተሰጠው ቢሆንም በተቃራኒው “የኛ ሰዎች የሚሉትን መስማት አለብን” በማለት መንፈሰ ጠንካራው ሙስሊም ህብረተሰብ በአወሊ ተገኝቷል፡፡ አወሊያ ዛሬም ከ100 ሺህ በላይ ሙስሊሞችን አስተናግዳለች፡፡ ዕለቱን በጉጉት ሲጠባባቅ የከረመው ሙስሊም ህዝብ አወሊያ መድረስ የጀመረው ገና በማለዳ ነበር፡፡የተለያዩ መልዕክት በሚያስተላልፉ መፈክሮች ያሸበረቀችው አወሊያ ምድረ-ጊቢው በቅፅበት ሰው በሰው ለመሆን በቃች፡፡ከመጀመሪያው የጁምዓ አዛን በኋላ ከመድረክ የተሰማውን የማስጠንቀቂያ መልእክት ተከትሎ ኢስላማዊ አንድነትን በማስመልከት በኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ የቀረበው በይዘቱ ለየት ያለ፣ ብዙሃኑን የማረከና ጠንካራ መልዕክት የተላለፈበት ዳዕዋ የዕለቱ መድረክ ፈር ቀዳጅ ሆኗል፡፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ በተለየ ሁኔታ ለአንድነትና ለመቻቻል በተለይም በዚህ ቀውጢ ቀን ከሙስሊሙ ኡማ የሚጠበቀውን ኃላፊነት በማስመልከት ያቀረበው ዳዕዋ ሚናው ከአስተማሪነት የላቀ ነበር፡፡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በታዳሚው ዘንድ ጉርምርምታ የፈጠረው የማይክራፎን ችግር የጥቂት ሰዎችን ሃሳብ መስረቁ አልቀረም፡፡

የጁምዓ ሰላት ተከትሎ የቀጠለው የዕለቱ ትዕይንት በርካታ ክንውኖችን አስተናግዷል፡፡ በዕለቱ አብዛኛው ተሳታፊ “መጅሊስ አይወክለኝም!” የሚል መልእክት ያዘለ “ባጅ” ደረት ላይ የለጠፈ ሲሆን በእጃቸውም ሳምንታዊ እና የተቃውሞው አካል የሆነቸውን “ድምፃችን ይሰማ” በራሪ መፅሄት ይዞ ተስተውሏል፡፡ በዕለቱ ከቀረቡ፣ በመፈክርና ተክቢራ ከታጀቡት የመድረክ ዝግጅቶች መካከል በሴት እህታችን አማካይነት የቀረበውና የሳምንቱን ውሎ የሚተነትን የአስተማሪነትና አዝናኝነት ይዘት የነበረው የዜና ዘገባ ይገኝበታል፡፡ይህን ተከትሎ ከእስከዛሬው ለየት ባለ መልኩ ህዝቡን በሃይለ ቃል የመፈክር ስሜት ይዞ የተጓዘውና በዶ/ር ኢብራሂም “አይሆንም!” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ንባብ ከፍተኛ መነቃቃትን ከመፍጠሩ በሻገር ፈፅሞ የማይረሳ ትዝታ ጥሎ አልፏል ማለት ይቻላል፡፡

ሰፊውን የመድረክ ሰዓት የወሰደው ዝግጅት ወቅታዊው የመጅሊስ ፕሬዝዳንት አቶ አህመዲን በራዲዮ ፋና ያቀረቡትን ተረት ተረት የተመለከተ ነበር፡፡ የግለሰቡን ውሸት የተሞላበት ንግግር ለህዝብ ግልጽ ከማድረግ ጋር በተያያዘ አወሊያን፣ ተማሪዎቹንና ውስጣዊ ስርዓቱን አስመልክቶ ከኮሌጁ ተማሪዎች መካከል ተማ ተውፊቅ የሰውዬውን ንግግር ሙሉ በሙሉ ውድቅ የሚያደርግና በመረጃ የታገዘ ማስተባበያ አቅርቧል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ አህመዲን አወሊያ ኦዲት የሚባል ነገር አያውቀም ሲል ያሰሙትን ውንጀላ አስመልክቶ ኡስታዝ ጀማል ያሲን ቁልጭ ያለ መረጃ ለህዝቡ በማስተላለፍ አራቁቷቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ አህመዲን መጅሊስን፣ የራሳቸውን ወደ ስልጣን አመጣጥ እና ምርጫን በማስመልከት የሰጡትን በውሸት የታጨቀ ንግግር ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በታሳታፊው ዘንድ አግራሞትን በጫረ ሁኔታ የሰውዬውን ንግግር ቃል በቃል ከጫወታ ውጭ አድርጓል፡፡

ሰፊ ህዝባዊ መሠረት ያለው የሙስሊሞች ተቃውሞ ህብረ ብሄራዊ ይዘትነቱን ያመላከቱና በትግሪኛና በኦሮሚኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የቀረቡት ሁለት ግጥሞች የአንድነት ስሜቱን ጥንካሬ ሰጥተውታል፡፡ አህባሽን ከቱርክ፣ የመን፣ሴኔጋል ወዘተ አገራት እናስመጣለን እያሉ መጅሊሶች ሰሞኑን እያራገቡት ያለውን ወሬያቸውን አስመልክቶ “እነኚ ሰዎች ማንን ነው የሚሸውዱት? ሊባኖስ መሰረቱን ያደረገውና በነዚህ አገሮች ቅርንጫፉን የዘረጋውን ቡድን የአገር ስም ለውጦ መልኩን ቀይሮ ሊያመጡት ነው፡፡” ሲል የመጅሊስን ተንኮል ያጋለጠው ታዋቂው ዳዒ ኡስታዝ በድሩ ነበር፡፡ አህባሾች ሱፍይ ነን እያሉ ያምታታሉ ሰዎች ተጠንቀቋቸው የሚል አዝናኝ ይዘት ያለው መልዕክት ታዋቂው “ደረሳው በከተማ” መነባንቡን አቅርቧል፡፡

የመጨረሻውና በኡስታዝ ሠይድ የቀረበውን ረዥም ዱዓ ተቀድሞ የቀረበው ፕሮግራም የኡስታዝ አቡበክር አህመድ ንግግር ነበር፡፡ በዋናነነት ትኩረት ሰጥቶ የነበረው በፋና ተጋብዘው የተቀረፀው የአንድ ሰዓት ከሃያ ዝግጅት ተዛብቶ፣ ሚዛናዊነት ጎድሎትና የተላለፈውን መልዕክት ገፍቶ የቀረበ መሆኑን በማስረዳት ነበር፡፡ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳደረባቸው ለአዘጋጁ መልዕክት ያስተላለፉ መሆናቸውን ገልጧል፡፡ በቀረጻ ፕሮግራማቸው ሂደት ያልዳሰሱት ተጨባጭ ሃቅ እንዳልነበረ ያስረዳው ኡስታዙ ህዝቡ የጣለባቸውን አደራ ሳያዛንፉ የጠራ መልዕክት በሚዲው በኩል እንዳስተላለፉ በአፅኖት አብራርቷል፡፡ ህዝቡም ይህንን ተረድቶ የግንዛቤ ማስተካከያ እንዲያደርግ መልዕክቱን ያስተላለፈው ኡስታዙ መንግስት ሚዲያውን ተጠቅሞ ያስተላለፈውን አጭርና አግባብነት ያለውን መልዕክት ለሰፊው ህዝብ ያላቸውን ከበሬታ ያሳያል በማለት ንግግሩን ቋጭቷል፡፡

የዕለቱ ዝግጅት እንከን አልባ ሆኖ በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላ ከአወሊያ እስከ ፓስተር አካባቢ የተመመው የህዝብ ጅረት በሠላም ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡

ድምፃችን ይሰማ!

Advertisements
 
3 Comments

Posted by on February 25, 2012 in Ahbash, Awelia, Dimtsachin Yisema, Majlis

 

3 responses to “አወሊያ 8ኛውን ሳምንት የህዝብ ተቃውሞ አስተናግ ዳዋለች!

 1. Feysel Redwan

  February 25, 2012 at 12:50 pm

  Allahu Akber!!! Allahu Akber!!! Allahu Akber!!! ahuneme ayehonem blenal.

   
 2. abdulkadir

  February 28, 2012 at 5:51 pm

  qen safubet

   
  • DimtsachinYisema

   February 29, 2012 at 1:44 am

   Wendim abdulqadir,
   Tsuhufi post yetederegebet qen postu lay silale betechemari qen metsafu asfelagi hono alagegnenewim,
   leasteyayetu enameseginalen.

    

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: