RSS

Category Archives: Dimtsachin Yisema

Please listen German Radio (DW); Discussion with Ahmedin Jebel, Akmel Negash, from Federal affairs Minster (ato Ewunetu), and Yusuf (East African affairs). http://www.dw.de/popups/popup_single_mediaplayer/0,,15498434_type_audio_struct_3076_contentId_3360782,00.html

 
 

‹‹ከቤተሰቧም መስካሪ (እንዲህ ሲል) መሰከረ›› ቁርዓን [ 12:26 ]

መንግስት በአህባሽ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ላይ ስለ ህገ መንግስቱ ከማስተማር የዘለለ ምንም ዐይነት ሚና እንዳልነበረው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴርና ሚኒስቴር ደኤታው እስኪሰለቸን ድረስ ሲደሰኩሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሰሞኑን የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በፌዴራላዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃይማኖትና የእምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጄነራል አቶ መረሳ ረዳን ጠቅሶ ያወጣው ዘገባ ግን ይህን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ አውቆም ይሁን በስህተት ራቁቱን አስቀርቶታል፡፡ ያንብቡት!

 
 

ወደ መጨረሻው ድል የመድረሳችን ማሳያዎች

ወደ ድል ጎዳና ያቀኑን ድሎቻችን በሚል ርዕስ በኛና በህዝባችን ውስጥ ማስረፅ የቻልነውን የድል አድራጊነት ስሜትና ማሳያዎቹን አይተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ በተቀናቃኝ ወገን ላይ ያሳደርነውን የተሸናፊነት ስሜት ለማየት እንሞክራለን፡፡ ለዚህም በዋናነት አህባሽንና መጅሊስን አስመልክቶ መንግስት እያሳየ ያለውን የአቋም መከረባበት እንደማስረጃ እንጠቀማለን፡፡

1. በህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞ መባቻ ላይ መንግስት በስልጠናው ላይ ጭራሽ እጁ እንደሌለበትና የመጅሊሱ ብቸኛ ስራ እንደሆነ ለማሳመን ጥረት አድርጎ ነበር፡፡ ለማዋያቁሽ ታጠኝ ሆነበት እንጂ!

2. ጣልቃ ገብነቱን የሚያሳዩ መረጃዎች በህዝቡ ዘንድ መኖራቸውን ሲያረጋግጥ ‹‹አዎን ለኢድ ሰላት ሰላም ለማስከበር እንደምንገኝ ሁሉ ስልጠና በተሰጠባቸው ቦታዎችም ሰላም ለማስከበርና ህገመንግስት ለማስተማር ተገኝተናል›› በማለት አቋማቸውን በተወሰነ ዲግሪ ዘንበል ማድረግ ጀመሩ፡፡ ከተነቃብን ማምለጫ እንፈልግ አይነት!!!

3. ‹ህግ ለማስከበር ሳይሆን ስልጠናውን እንደ ሃገር አቋም አድርጋችሁ ሁሉም ሊከተለው እንደሚገባ ስታስተዋውቁ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለን› ተብለው ሲሞገቱና ሲረቱ ‹‹ማንም በግድ የሰለጠነ የለም እኛም በመጅሊስ መረጃ እና ጋባዥነት ነው የተሳተፍነው›› በማለት ከዘጠና ዲግሪ ያላነሰ መዘንበል አሳዩ፡፡

4. ‹በግድ ለማሰልጠኑማ ይህንን ከእስልምና ያፈነገጠ አስተምህሮ በመቃወም የተባረሩ ኢማሞች፤ የተዘጉ መድረሳዎች፤ አልሰለጥንም በማለታቸው የታሰሩትን ቤቱ ይቁጠረው›› ተብለው ሲሞገቱ አስገራሚ እና አሳዛኝ የሆነ የአቋም ለውጥ በማምጣት ‹‹ ስልጠናውን ከመጅሊስ ጋር በመሆን በጋራ አስተባብረናል አስተምህሮቱም የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከ1400 አመት በፊት ይከተሉት የነበረውን ነው ያሰለጠንነው ብለው አረፉት›› ለመሆኑ ፖለቲካቸው እንዳያር ማገላበጥ ሲኖርባቸው የእምነት ጉዳያችን ውስጥ ገብተው እንዲህ ማቡካታቸው ምን ይሉታል፡፡ እውን የኢትዮጵያ ሙስሊም ከክርስቲያን ጎረቤቱ እየሰረቀና ቁማር እየተጫወተ፤ ሃላል ሃራሙን እያደበላለቀ፤ በወለድ ተጨመላልቆ፤ ሂጃብ ለምኔ በማለት እርቃኑን የኖረ፤ በአቋም የተለየውን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ እያከፈረ ……የኖረ ነው እንዴ? ታዲያ በጋራ ያስተባበሩት ስልጠና አስተምህሮው እነዚህን ሁሉ ነገሮች ሃላል አድርጎ ሳለ የኢትዮጵያ ሙስሊም ሲከተል የኖረውን ነው ያሰለጠንነው በማለት ስለምን ይሳለቁብናል? ሆኖም ግን ለጣልቃ ገብነታቸው ሙሉ በሙሉ እጅ ሰጥተዋል!!

5. ‹‹ጣልቃ መግባታችሁን ካመናችሁ እንደአገባበችሁ ሁሉ በይፋ ውጡ›› ሲባሉ ደግሞ ‹‹ እኛ ሃገር የሚገኘው ውሃብያ ሳኡዲ ከሚገኘው ይለያል ካሉ እኛ ስራችንን ጨረስን ማለት ነው እንስማማለን›› በማለት ሲፈተፍቱ መኖራቸውን ዳግም በማረጋገጥ ለእነሱ መውጫ የመሰላቸውን ለእኛ ግን አደገኛ መርዝ ለመዝራት ከጀሉ፡፡ እኛ ደግሞ አቋማችን ‹ወይ ፍንክች! አህባሽ በመጅሊሳችን አስተባባሪነት ሊሰጥ አይገባውም መንግስትም ያለምንም ሰበብ እጁን ያውጣ› እኛ ሙስሊሞች ነን አህባሽ ብቻ ከመሃላችን ይውጣልን በማለት ላይ እንገኛለን፡፡

6. ‹ ለዚህ ሁሉ ምክንያት የሆነውም መጅሊስ ባስቸኳይ በምርጫ ይተካ› ለሚለው ሙግታችን ‹‹በዴመክራሲያዊ ስርዓት ስልጣን በምርጫ እንደሚያዝ እናምናለን ሆኖም ግን የራሱ አሰራር አለውና መንግስት ጣልቃ መግባት አይችልም በሰልፍም የሚፈጠር ነገር የለም›› ሲሉ ቀለዱ፡፡ ቀጠል አርገውም ‹‹ በአሁን ሰአት ምርጫ ይካሄድ ቢባል ወሃብያ ለስልጣን አሰፍስፎ ስለሚገኝ በጭራሽ አሁን አይካሄድም›› ሲሉ ደረቅ አቋም አንፀባረቁ፡፡

7. የህዝበ ሙስሊሞ ተቃውሞ የአንድ ሰሞን ጩኸት ብቻ እንዳልሆነ ሲረዱና መውጫ ሲያጥራቸው ‹‹ ምርጫው በአፋጣኝ ይካሄዳል መንግስትም ማድረግ የሚችለው ድጋፍ ማድረግ ስለሆነ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን›› በማለት ያ! ብዥታ ያለበት መልሳቸውን ሰጡ፡፡

ከላይ ያየናቸው ነጥቦች ሁሉ በእስካሁኑ ጉዟችን ድል አድራጊነት እንዳልተለየን ማሳያዎች ናቸው፡፡ ታዲያ በኛ በኩል የሚጠበቀው ትልቁ ነገር የምንፈልገው ውጤት እንጂ ሂደት ብቻ ባለመሆኑ ግልፅ ውጤት እስከሚመጣ በፅናትና በአንድነት መታገል ነው፡፡ የትግላችን መሰረት የሆነው የአወሊያ ትዕይንተ ህዝባችን ለማንም እንደማንንበረከክ በሚያሳይ መልኩ መቀጠል ሲኖርበት ክልሎችም የተቃውሞ ፊርማ አሰባስባችሁ መምጣታችሁ እሰየው የሚባል ሆኖ እያለ መሰል ትዕይንቶችን በየአካባቢያችሁ ልታደርጉ ይገባል፡፡ እስከ አሁን አንዳችም ሙከራ ሳይደረግብንና ሳንፈተን እነዚህን ሁሉ ድሎች ከተጎናፀፍን በቀጣዮቹ ግዚያት በጥቂት መሰዋእትነት ጥቄዎቻችን ሳይሸራረፉ እንደሚመለሱልን አንጠራጠር፡፡ ፅናት እና አንድነት ግን ቁልፍ ሚስጥር ናቸው፡፡ አላሁ አዕለም፡፡

 
 

ወደ ድል ጎዳና ያቀኑን ድሎቻችንን

ከፊሉ ህዝበ ሙስሊም የየካቲት 26 ቀጠሮን የትግሉን ፍሬ የምናጣጥምበት የነፃነት ቀን አድርጎ ይቆጥረው ነበር፡፡ ከፊሉ ምናልባትም ደግሞ ብዙሃኑ ስሊም ግን የትግሉ ዛፍ ገና የሚተከልበት እለት እንደሆነ በማሰብ ፍሬውን አሻግሮ የሚያልም ነበር፡፡ ‹‹ አስቀድሞ የበሰለ ፍሬ አስቀድሞ ይቆረጣል›› እንደሚሉት ብሂል የትግል ፍሬአችንም ፈጥኖ እንዳይቆረጥ ተፈጥሮአዊ ሂደቱን ጠብቆ እየጎመራ ይገኛል፡፡ አንዳንዶች በፍርሃት በተሸበበ ስሜትና የመንግስት የዜጎቹን መብት የማስከበር ኃላፊነትን በአጉል ጨለምተኝነት በመጠራጠር የትግል ፍሬአችን መጎምራቱን ይጠራጠራሉ፡፡ ለዚህ ጥርጣሬ ከንቱነት እስከ አሁን የተጎናፀፍናቸው ድርብ ድርብርብ ድሎች ማሳያ ናቸው፡፡

  1. ከጥቂት ወራት በፊት ስለ አህባሽም ሆነ ስለመጅሊስ ማውራት ሳይሆን ማሰብ የተከለከለ በሚያስመስል ሁኔታ በፍርሃት የተሞላን ነበርን፤
  2. በግል ወሬና በየፌስቡኩ ‹‹ ተገናኝቶ ጉዳያችንን የሚመክር አካል ያስፈልገናል›› እያልን ጥቂት ግለሰቦችን የምንናፍቅ ደካሞች ነበርን፤
  3. በአወሊያ ካሳለፍናቸው ሳምንታት የመጀመሪያዎቹ 2 እና 3 ጁምዓዎች ‹‹ ጥቂት ግለሰቦች››፤ ፅንፈኞችና አክራሪዎች››፤ በተማሪዎች ጥየቄ ሽፋን የግል የፖለቲካ አቋማቸውን የሚያራምዱ››……….በሚሉ ቅፅል ስሞች በሚዲያዎች የምንታማ ነበርን፤

ዛሬስ?

  1. አህባሽም ሆነ መጅሊስ በአደባባይ ማውገዝ ከመቻላችን በላይ አፍ በወጉ ያልፈቱ ህፃናት ሳይቀር ‹‹መጅሊስ አይወክለንም›› ማለት እስኪችሉ ድረስ ጠላታችንን እየተፋለምን ነው፡፡ አልሃምዱሊላህ!!
  2. ጥየቄአችንን ለማስመለስ ብልሃት የተሞላባቸው አካሄዶችን በመከተል ፈርተን ከተደበቅንበት ዋሻ ወጥተን ከመንግስት አካላት ጋር በመወያየት ላይ እንገኛለን፡፡ ሱመ አልሃምዱሊላህ!!
  3. ንቀው ያስናቁንን እና በራቸው ዝግ የነበሩትን የመጅሊስ አመራሮችን ለድርድር በየሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማንከራተት ችለናል፤
  4. ከምንም በላይ ያለማንም ቀስቃሽ መብቱን መጠየቅ የሚችል በአንድ ጁምዓና በአንድ ቦታ መቶ ሺዎችን ማሰባሰብ ችለናል፤
  5. ትግሉ መቼም ሊቋረጥ በማይችል መልኩ በማንኛውም ቅፅበት እና በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል ሊቀጣጠል የሚያስችል ሃገር አቀፍ ህዝባዊ መሰረት መጣል ችለናል፤
  6. በቀጣይ ምላሽ እንደምናገኝ ባንጠራጠርም መልስ ሊሰጠን የሚገባው መጅሊስ ሳይሆን መንግስት እንደሆነ ህዝበ ሙስሊሙ አምኗል፡፡ በመሆኑም የጥየቄዎቻችን መመለስ በህዝበ ሙስሊሙ እና በመንግስተ መካከል የመተማመንና የመደጋገፍ ስሜትን ሲያዳብር ጥያቄዎቻችንን ማስተባበል ደግሞ ተቃራኒ ስሜት መፍጠሩ እርግጥ ነው፡፡

በመሆኑም እነዚህና ሌሎች ድሎቻችን ለውጤት መቅረባችንን አመላካች ናቸው፡፡ ነገር ግን ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ የአላማችን ፅናት የሚፈተንበት፤ ለዲናችን ያለን ተቆርቋሪነት በተግባር የሚታይበት ጊዜ ከመቼውም በላይ በመቃረብ ላይ ይገኛል፡፡ ይህ ትውልድ በዘመኑ ሃገራዊ የታሪክ ግድፈት እንዳይፈጠር ዘብ እንደሚቆም ታሪክ የሚዘክረው ስራ ሰርቶ እንደሚያልፍ መስካሪ አያሻም፡፡ ነገም በአላህ ፊት በዚህ አኩሪ ታሪክ ተወዳሽ እና ምንዳ ተከፋይ እንደሚሆን ተስፋ ሰንቋልና ወደ ኋላ የሚልበት ግዜ አልፏል፡፡ ሁሉም ሙስሊም በነፍስ ወከፍ ‹‹ እኔ እያለሁ በዲኔ ላይ ጉድለት አይታይም›› የሚል ኢስላማዊ መርህ አንግቦ ከውጤት ውጪ ወደቤቴ የሚመልሰኝ የለም ይላል፡፡ ድል ለሙስሊሞች! አላሁ አክበር!አላሁ አክበር!አላሁ አክበር!

 
4 Comments

Posted by on March 15, 2012 in Ahbash, Awelia, Dimtsachin Yisema, Majlis

 

ውዝግቡ ቀጥሏል! እርስዎስ ምን ይላሉ?

ከትላንት ወዲያ በኦሮሚያ ክልል ደራ ከተማ ውስጥ መውሊድን በማክበር ሽፋን አቶ አህመዲን አብዱላሂን እና አቶ ዓዛምን ጨምሮ የክልል መጅሊስ ተወካዮች በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡ “አብሽሩ”፣ “የምትሰሙትና የሚወራው ነገር በሙል ትርጉም የሌሽ ነው”፣ “መንግስት ከኛ ጋር ነው”፣ “እንደሚደግፈን ቃል ገብቶልናል”፣ “በ15 ቀናት ውስጥ ስልጠና መስጠታችንን እንቀጥላለን እናንተም በሚስጥር ሰዎችን መልምላችሁ አዘጋጁ” …ወዘተ በማለት አቶ አህመዲን ለተገኘው ሰው ንግግር አድርጓል፡፡

የጥፋት ወጥመዳቸውን በመተብተብ ላይ በነበሩበት ቦታ የፌዴደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ዶ/ር ሽፈራው አቶ አህመዲን ባስቸኳይ ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ይደውልለታል፡፡ ሰውዬውም እየተጣደፍ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት በመነሳት አዲስ አበባ ይገባል፡፡ በማግስቱ /ሰኞ/ ጧት አራት ሰዓት ላይ ከተገናኙ በኋላ ዶ/ሩ ቀጭን ትዕዛዝ የሚያስተለልፍ ደብዳቤ በእጁ ይሰጠዋል፡፡ ከዚህ በፊት እናንተ መጅሊሶች ወሃቢያንና ሌሎች ከሽብርና ፅንፈኝነት ጋር የተየያያዙ ጉዳዮችን እያነሳችሁ የነገራችሁንን ነገር በሙሉ አምነን በመቀበል በስልጠና መድረኮቻችሁ ሳይቀር የናንትን ቃል እንደ ገደል ማሚቶ ስናስተጋባ ቆይተናል፡፡ ሆኖም የምታወሩትና የምታስወሩት ነገር ምን ያክል እውነትነት እንዳለውና ተጨባጭ እንደሆነ ማስረዳት የሚችል መረጃ አዘጋጅታችሁ አሁን ባስቸኳይ አቅርቡ፡፡ በዚህም ወሃቢያ የምትሉትን በሚገባ አብራርታችሁ፣ አክራሪ ነው፣ አሸባሪ ነው፣ ፀረ ህገ መንግስት ነው፣ ፀረ ህዝብና ፀረ መቻቻል ነው ስትሉ ምን ማለታችሁ እንደሆነ ተጨባጭነት ያለው ሰነድ አቅርቡ የሚል ይዘት ያለው Read the rest of this entry »

 
1 Comment

Posted by on February 28, 2012 in Dimtsachin Yisema, Majlis

 

ያልሰማ ይስማ! የሰማ ያሰማ!

ከታማኝ ምንጮች የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት መንግስት የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄዎች በሚገባ ተደርቻለሁ፣ ምላሽ ልሰጥባቸው ይገባል በማለት ላይ ይገኛል፡፡ ፍፁም ሰላማዊና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የጠበቀ የመብት ጥያቄያችን አካሄዱ ከፍተኛ አድናቆት ያገኘ መሆኑ የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ግፊቱ የበረታ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ መንግስት ጥያቄዎቻችንን ምላሽ ለመስጠት ዳር ዳር በሚልበት በዚህ ሰዓት ከሚወስዳቸው የመፍትሄ እርምጃዎች አንዱ ምርጫ ማካሄድ የሚለው ይገኝበታል፡፡ ወቅታዊ የሙስሊሞችን ጉዳይ አስመልክቶ ኢህአዴግ እንደ ድርጅት እስካሁን ባካሄዳቸው የውይይት መድረኮች እንደተገለፀው ፍትሐዊ ምርጫ ማካሄድ ሁነኛ የመፍትሄ አቅጣጫ እንደሆነ ታምኖበታል፡፡ እስካሁን ይዘውት በቆዩት አቋም መቀጠል እንደሌለባቸውም አምነዋል፡፡ ስለዚህ የአሁኑ የመጅሊስ አመራሮች ተወግደውና የሽግግር ጊዜ የሚባል አካል ተዋቅሮ ምርጫውም የራሳቸው የሚባሉ ሰዎችን በማካተት እንዲካሄድ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ከዚህ በመነሳት በዚህ የምርጫ ሂደት ውስጥ ሊሳተፉ የሚገባቸው ተብለው የተለዩ አካላት የሚከተለውን መስፈርት መሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

• ነፃ አመለካከት ያለው/ሊበራል አስተሳሰብ ያለው፣
• ወሃቢያ ያልሆነ፣
• አዲስ ፊት /ከዚህ ቀደም በዚህ ስርዓት ውስጥ የማይታወቅ/፣
• ከኢህአዴግና ከመንግስት ጋር መስራት የሚችል፣
• ተሠሚነት ያለው፣ ተናግሮ ማሳመን የሚችል፣
• የብሔር ብሔረሰብ ተዋፅኦ ያለበት እና የመሳሰሉት ይገኙባቸዋል፡፡

በዚህም መሠረት እነኚህን መስፈርቶች ሊያሟሉ የሚችሉ ግለሰቦችን እንዲጠቁሙ የቤት ስራ የተሰጣቸው አካላት እንዳሉ ታውቋል፡፡ ይህንን በማስፈፀም ሂደት መስጂዶችና የመስጂድ አካባቢዎች ዋነኛ ማዕከል እንደሚሆኑ የታመነበት ሲሆን ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሁኔታውን በጥብቅ እንዲከታተለው ከፍተኛ ፍላጎት አለን፡፡ Read the rest of this entry »

 
3 Comments

Posted by on February 27, 2012 in Dimtsachin Yisema, Majlis

 

የመብት ጥያቄያችን ጠንካራ ህዝባዊ መሠረት መያዙ ዛሬም በድጋሜ ተረጋገጠ!

የዛሬውን የስብሰባ ውሎ መረጃ እንደደረሰን ለአንባቢዎቻችን እናደርሳለን ባልነው መሰረት ትኩስና ያልተበረዘ ወሬችንን እንካችሁ ብለናል፡፡

የጥሪ ደብዳቤው ስብሰባው 2፡30 እንደሚጀምር ቢጠቅስም የአዳራሹ ሁለት እርከኖች በሰው ብዛት ጢም ብሎ ስብሰባው የተጀመረው 3፡20 ላይ ነበር፡፡ መድረኩ ላይ የከተማው ከንቲባ የተከበሩ ኩማ ደመቅሳ እና የከተማው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊና የከንቲባው አማካሪ አቶ ጌታቸው አምባዬ ተሰየሙ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉትን ችግሮች በተመለከተ ከእናንተ ጋር መወያየት ስለፈለግን ነው የጠራናችሁ በማለት መድረኩ ተከፈተ፡፡ የተከበሩ ከንቲባ የመጀመሪያውን እድል ወስደው ሲያበቁ በሀገራችን ያለውን  አኩሪ የመቻቻል ታሪክ፣ ችግሮች ሲፈጠሩ መፍትሄ የተፈለገባቸውን አካሄዶች፣ ውጤታቸውን እና ሌሎች ተዛማጅነት ያላቸውን ነጥቦች በማንሳት ከዚህ አንፃር ጠቅለል ባለ ሁኔታ የመንግስትን አቋም አንፀባርቀዋል፡፡ ከህግና ስርዓት አንፃር ተጨማሪ የመንግስትን አቋም የማብራራት ተራውን የወሰዱት አቶ ጌቸው በኢትዮጵያ የትኛውም ሐይማኖት እኩል እንደሆነና እኩል መብት እንዳለው፣ መንግስት በሐይማኖት ሐይማኖት በመንግስት ጣልቃ እንደማይገባ በዚህ ረገድም መንግስት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንደሚያደረግ፣ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ከሐይማኖቶች አንፃር ችግሮች እየተከሰቱ እንደሆነና የሐይማኖት መብቶች የህዝብን ሠላም ከመጠበቅ… አኳያ  ሊገደቡ እንደሚችሉ ገለፃ ከሰጡ በኋላ መድረኩ ለተሳታፊው ውይይት ክፍት ሆነ፡፡ ከተሰብሳቢው መካከል የቀድሞ የመጅሊስ አመራሮች መካከል እንደ ኢልያስ ሬድማንና አቶ ተሻለ የመሣሰሉ ግለሰቦች መኖራቸውን የተረዳው ጠቅላላ ተሰብሳቢ እነኚህ ሰዎች ያልተገባ ዕድል ተሰጥቷቸው የመድረኩን መንፈስ ያውኩታል፣ ይበጠብጡታል በዚህም መድረኩ ባልታሰበ ሁኔታ ይዘቱ ይለወጣል የሚል ስጋት አድሮባቸው ነበር፡፡ መድረኩ ለውይይት ክፍት በሆነበት ቅፅበት ሀሳብ መስጠት የፈለገው ተሳታፊ እጅ በርካታ በመሆኑ ሁኔታዎች በቅፅበት መልካቸው ተቀየረ፡፡ Read the rest of this entry »

 
1 Comment

Posted by on February 26, 2012 in Ahbash, Dimtsachin Yisema, Majlis

 

አወሊያ 8ኛውን ሳምንት የህዝብ ተቃውሞ አስተናግ ዳዋለች!

የሙስሊሙ ጥያቄዎች መልስ ሊሰጥባቸው ለየካቲት 26 ቀጠሮ በተያዘበት ሁኔታ አወሊያ በዛሬው ዕለት ባልተጠበቀ የህዝብ ማዕበል ተጥለቀለቀች፡፡ በዕለተ ረቡዕ ምሽት ራዲዮ ፋና ያስተላለፈው ሚዛናዊነት የጎደለው ፕሮግራም የብዙሃንን ቀልብ ሰብሮ ከተቃውሞ የትዕይንት መድረኩ ያርቃቸዋል የሚል ግምት የተሰጠው ቢሆንም በተቃራኒው “የኛ ሰዎች የሚሉትን መስማት አለብን” በማለት መንፈሰ ጠንካራው ሙስሊም ህብረተሰብ በአወሊ ተገኝቷል፡፡ አወሊያ ዛሬም ከ100 ሺህ በላይ ሙስሊሞችን አስተናግዳለች፡፡ ዕለቱን በጉጉት ሲጠባባቅ የከረመው ሙስሊም ህዝብ አወሊያ መድረስ የጀመረው ገና በማለዳ ነበር፡፡የተለያዩ መልዕክት በሚያስተላልፉ መፈክሮች ያሸበረቀችው አወሊያ ምድረ-ጊቢው በቅፅበት ሰው በሰው ለመሆን በቃች፡፡ከመጀመሪያው የጁምዓ አዛን በኋላ ከመድረክ የተሰማውን የማስጠንቀቂያ መልእክት ተከትሎ ኢስላማዊ አንድነትን በማስመልከት በኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ የቀረበው በይዘቱ ለየት ያለ፣ ብዙሃኑን የማረከና ጠንካራ መልዕክት የተላለፈበት ዳዕዋ የዕለቱ መድረክ ፈር ቀዳጅ ሆኗል፡፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ፈረጅ በተለየ ሁኔታ ለአንድነትና ለመቻቻል በተለይም በዚህ ቀውጢ ቀን ከሙስሊሙ ኡማ የሚጠበቀውን ኃላፊነት በማስመልከት ያቀረበው ዳዕዋ ሚናው ከአስተማሪነት የላቀ ነበር፡፡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በታዳሚው ዘንድ ጉርምርምታ የፈጠረው የማይክራፎን ችግር የጥቂት ሰዎችን ሃሳብ መስረቁ አልቀረም፡፡

የጁምዓ ሰላት ተከትሎ የቀጠለው የዕለቱ ትዕይንት በርካታ ክንውኖችን አስተናግዷል፡፡ በዕለቱ አብዛኛው ተሳታፊ “መጅሊስ አይወክለኝም!” የሚል መልእክት ያዘለ “ባጅ” ደረት ላይ የለጠፈ ሲሆን በእጃቸውም ሳምንታዊ እና የተቃውሞው አካል የሆነቸውን “ድምፃችን ይሰማ” በራሪ መፅሄት ይዞ ተስተውሏል፡፡ በዕለቱ ከቀረቡ፣ በመፈክርና ተክቢራ ከታጀቡት የመድረክ ዝግጅቶች መካከል በሴት እህታችን አማካይነት የቀረበውና የሳምንቱን ውሎ የሚተነትን የአስተማሪነትና አዝናኝነት ይዘት የነበረው የዜና ዘገባ ይገኝበታል፡፡ይህን ተከትሎ ከእስከዛሬው ለየት ባለ መልኩ ህዝቡን በሃይለ ቃል የመፈክር ስሜት ይዞ የተጓዘውና በዶ/ር ኢብራሂም “አይሆንም!” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው የግጥም ንባብ ከፍተኛ መነቃቃትን ከመፍጠሩ በሻገር ፈፅሞ የማይረሳ ትዝታ ጥሎ አልፏል ማለት ይቻላል፡፡

ሰፊውን የመድረክ ሰዓት የወሰደው ዝግጅት ወቅታዊው የመጅሊስ ፕሬዝዳንት አቶ አህመዲን በራዲዮ ፋና ያቀረቡትን ተረት ተረት የተመለከተ ነበር፡፡ የግለሰቡን ውሸት የተሞላበት ንግግር ለህዝብ ግልጽ ከማድረግ ጋር በተያያዘ አወሊያን፣ ተማሪዎቹንና ውስጣዊ ስርዓቱን አስመልክቶ ከኮሌጁ ተማሪዎች መካከል ተማ ተውፊቅ የሰውዬውን ንግግር ሙሉ በሙሉ ውድቅ የሚያደርግና በመረጃ የታገዘ ማስተባበያ አቅርቧል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ አህመዲን አወሊያ ኦዲት የሚባል ነገር አያውቀም ሲል ያሰሙትን ውንጀላ አስመልክቶ ኡስታዝ ጀማል ያሲን ቁልጭ ያለ መረጃ ለህዝቡ በማስተላለፍ አራቁቷቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ አህመዲን መጅሊስን፣ የራሳቸውን ወደ ስልጣን አመጣጥ እና ምርጫን በማስመልከት የሰጡትን በውሸት የታጨቀ ንግግር ኡስታዝ አህመዲን ጀበል በታሳታፊው ዘንድ አግራሞትን በጫረ ሁኔታ የሰውዬውን ንግግር ቃል በቃል ከጫወታ ውጭ አድርጓል፡፡ Read the rest of this entry »

 
3 Comments

Posted by on February 25, 2012 in Ahbash, Awelia, Dimtsachin Yisema, Majlis

 

በስዊድን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሙስሊሞች እያደረጉት ላለው የመብት ጥያቄ ድጋፍ አደረጉ።

ባለፈው ሳምንት እለተ እሁድ 19/02/2012 በስዊድን ስቶኮልም የሚገኘው ነጃሺ የኢትዮጲያውያን ሙስሊሞች ማህበር ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እያደረጉት ያለውን የመብት ጥያቄ በመደገፍ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት አደረገ። በስብሰባው የተገኙት ተሰብሳቢዎች የአህባሽ አስተምህሮት ምን እንደሆነና ከሙስሊሞች አስተሳሰብ ጋር ያለውን መሠረታዊ ልዩነት ለማሳየት ሞክረዋል። አሕባሽ በዚህ ከቀጠለም ሙስሊሙን በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደሚከተው አስታውሰዋል። መጅሊስ አህባሽን በግድ በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ለመጫን የሚያደርገውን ጥረት እንዲያቆም በማለትም ተሳታፊዎቹ አሳስበዋል። መንግስትን በመወከል በስብሰባው የተገኙት የኢፌዴሪ የስዊድን ቆንስላ ዋና ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ መብራቴ እና የስራ ባልደረባቸው ወ/ሮ ሮማን አብዱልቃድር ሲሆኑ ከተሳታፊው ህዝብ የቀረበላቸውን ጥያቄ የሚችሉትን ያህል የመለሱ ሲሆን ከነሱ አቅም በላይ የሆነውን ለሚመለከተው የበላይ አካል እንደሚያስተላልፉ ገልፀዋል።

በመጨረሻም ተሰብሳቢዎቹ በነጃሺ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር ስም ለጠ/ሚኒስተር መለስ ዜናዊ የተፃፈ ደብዳቤ እንዲያደርሱላቸው ደብዳቤ አስፈርመው ለሃላፊዎቹ አስረክበዋቸዋል። ደብዳቤውም የወቅቱን የሙስሊሙን ህብረተሰብ ጥያቄዎች አካትቷል። ከጥያቄዎቹም መሀል የአህባሽ አስተምህሮ እንደማንኛውም አስተምህሮ ማስተማር የሚችሉ ቢሆንም የህዝበ ሙስሊሙን የእምነት ተቋም መጠቀም እና ኢማሞችን ማባረር ህገ መንግስቱን የሚፃረር ተግባር በመሆኑ የአህባሽን አስተሳሰብ በግድ የማጥመቅ ዘመቻ እንዲቆም ጠይቀዎል። 2) መጅሊስ ሙስሊሙን የማይወክሉ የሙስሊሙን እድገት የጎተቱ እንዲሁም ቁልቁል ወደታች ያደረጉ አመራሮች የተሞላ በመሆኑ ህዝበ ሙስሊሙ በሚወክላቸው እና ተቀባይነት ባላቸው ግለሰቦች በህዝበ ሙስሊሙ ምርጫ እንዲተኩ 3) በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚደርስባቸው በደልና እንግልት እንዲቆም 4) በአወሊያ ለተመረጡት አስራ ሰባቱ ኮሚቴዎች እውቅና እንደሚሰጡና የመጅሊስ አመራሮችን በህዝቡ በተመረጡ ተወካዮች እንዲተኩ ለሚያደርጉት ጥረት ለኮሚቴዎቹ ያላቸውን ሙሉ ድጋፍ ገልፀዋል።

 
Leave a comment

Posted by on February 24, 2012 in Ahbash, Dimtsachin Yisema, Majlis

 

ሙእሚን ሆይ! አትቆጣ!

አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ። ወዳጄ እነሆ ከአወሊያ ተማሪዎች የተረከብከው የመብት ማስከበር ትግል 8ኛ ሳምንት ላይ ደረስክ። አላህን አመስግን። ባለፉት ሳምንታት ባደረግከው ተጋድሎ አላህ ድልን እያስጨበጠህ ነው። ኢንሻ አላህ በአኼራም እጥፍ በእጥፍ ይክስሃል። ሁሉም የመጣው ከአላህ እንደመሆኑ አስደሳች ውጤትንም የሚሰጥህ አላህ ብቻ ነው። በአላህ መንገድ ለተጓዘ እውነትን ፍለጋ ጊዜውን፣ ገንዘቡን፣ ጉልበቱን የሚያውል አላህ በአዱንያም በአኼራም ያስደስተዋል።

ታዲያ ለሃቅ የምታደርገው ትግል፣ ለዲንህ የምትከፍለው መስዋእትነት የሚያበግናቸው፣ ጥቅማቸው የሚነካ የሀሰት ደቀ መዛሙርት እንደሚናደዱብህና ከወዳጃቸው ሰይጣን ጋር እንደሚዶልቱብህ አትዘንጋ! እነዚህ ሰዎች ከዑማው ጥቅም ይልቅ የከርሳቸውን መሙላት ነው የሚስቀድሙት። ዲነል ኢስላም፣ በአላህ መንገድ መታገል፣ የሙስሊሞችን ሐቅ ማስጠበቅ ለነሱ ፌዝ ነው። ያንተ ጩኸት፣ ያንተ ነጋ ጠባ ለዲንህ መታገል የእነሱን ጥቅም ስለሚያስቀርባቸው ሊያሰናክሉህ ይፈልጋሉ። ቢችሉ አደናብረው፣ ካልሆነ ታግለው ሊያንበረክኩህ ይፈልጋሉ። ከአላህ መንገድ ስለራቁ ‹ሃይል አለው› ብለው ከሚያምኑት ወገን ተጠግተው በአጭር ሊያስቀሩህ ይፈልጋሉ።

ዘዴያቸው ብዙ ነው። የመጀመሪያው ባንተ ላይ ሽብር መንዛት ነው። አንተን ጸረ-ሰላም፣ ጸረ-ልማት አድርገው ይስሉሃል። ይሄ ካልተሳካላቸው ከወንድሞችህ ጋር የፈጠርከውን ህብረት ለመበጣጠስ ይጥራሉ። ለአንተ መጥተው የወንድምህን መጥፎ ገጽታ ይስሉልሃል። ለሱም ያንተን መጥፎ ገጽታ ያቀርቡለታል። ይሄ ካልተሳካላቸው ያስፈራሩሃል። በአደንቋሪ ጩኸት ሊያስበረግጉህ ይፈልጋሉ። አልሃምዱሊላህ! አንተ ለነዚህ ሁሉ አልተበገርክም። ባለፉት ሰባት ሳምንታት ከላይ የጠቀስኩልህን ሁሉ አድርገውብህ አልበገርም ብለሃቸው በንዴት ጦፈዋል። አሁን የቀራቸውን የተንኮል መረብ እየዘረጉብህ ነው። ይኸውም በስድብ፣ በንቀት፣ በመጎሸም ተናደህ ሸይጧን እንዲጠጋህ ይፈልጋሉ። Read the rest of this entry »

 
3 Comments

Posted by on February 24, 2012 in Awelia, Dimtsachin Yisema, Majlis

 
 
Follow

Get every new post delivered to your Inbox.

Join 35 other followers